🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 1/2018 (ኢዜአ)፦ የመደመር መንግሥት እይታ በሁለንተናዊ ዘርፍ ወደፊት ለመስፈንጠር የሰለጠነ የሰው ሃይል ግንባታ ላይ ትኩረት ማድረጉን የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት፤ የመደመር መንግሥት የነበሩ ጥንካሬዎችንና ክፍተቶችን በመለየት ጥንካሬዎችን በተሻለ መልኩ የሚያስቀጥልና ክፍተቶችን ደግሞ በዘላቂነት የሚቀርፍ እሳቤ ነው፡፡
የመደመር መንግሥት እሳቤ ምርትና ምርታማነት በሚፈለገው ፍጥነትና መጠን አለማደጉን ከኢኮኖሚ ስብራቶቻችን መካከል አንዱ አድርጎ ይቆጥራል ብለዋል፡፡
እሳቤው ይህንን ስብራት በዘላቂነት ለመጠገን በተለያዩ ዘርፎች ብቁ የሰው ሃይል መገንባት አስፈላጊ መሆኑን ያምናል ነው ያሉት፡፡
የብልጽግና ራዕይን እውን ለማድረግ የሰው ሃይል ግንባታን ልክ እንደ ካፒታል እና የተፈጥሮ ሃብት ይመለከታል ብለዋል፡፡
የኢንዱስትሪ፣ የግብርና፣ የማዕድን፣ የቱሪዝምና የሌሎች ዘርፎችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በተለያዩ የሙያ መስኮች የሰለጠ የሰው ሀይል መገንባት በእጅጉ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
ባለፉት የለውጥ ዓመታት በሰው ሃይል ግንባታ እመርታዊ ለውጥ ለማምጣት በተለይም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማትን ደረጃቸውን የማስጠበቅና የማስፋፋት ስራ ላይ በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን ጠቁመዋል፡፡
አዳዲስ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ተዘጋጅተው ስራ ላይ መዋላቸውንም አመላክተዋል፡፡
የትምህርት ስርዓቱ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው ለጥራት ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ይህም የዜጎችን ዓለም-አቀፍ ተወዳዳሪነት እያሳደገው እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
በዚህም ወጣቶች ከሥራ ፈላጊነት በመላቀቅ ሥራ መፍጠር ላይ ትኩረት ማድረግ መጀመራቸውን ነው የጠቆሙት፡፡
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ንግድና ኢንቨስትመንት ስኬት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ ውጤት ማሳያ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ...
Mar 27, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ አህጉራዊ የኢንቨስትመንት ማዕከልነትን እያረጋገጠ ...
Mar 26, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025