
አዲስ አበባ፤ ታኀሣሥ 26/2017(ኢዜአ)፦ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ኢትዮ ቴሌኮም የዲጂታል ኢትዮጵያ ሽግግርን ለማፋጠን በሚያስችሉ ተግባራት ላይ መከሩ።
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ/ር ) የኢትዮ ቴሌኮም ኤክስፒሪየንስ ማዕከልን የጎበኙ ሲሆን ከኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ጋር ተወያይተዋል።
ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ኢትዮ ቴሌኮም ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ግንባር ቀደም ሚና የሚጫወት ተቋም ነው ብለዋል።
ኩባንያው በዲጂታል አገልግሎቶች እና ቴሌብር አስደማሚ ውጤት በእያስመዘገበ ስለመሆኑም ገልጸዋል።

ዲጂታል አገልግሎት ተደራሽነትና አካታችነት በመጨመር ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በሚያስችሉ የኢጋቨርንመንት፣ ኢኮሜርስ፣ ኢኖቬሽን፣ በጀማሪ የሥራ ፈጠራ፣ ጥናትና ምርምር፣ ስማርት ስልክ ስርጸት እና የዲጂታል ክህሎትን ለመሻሻል በቅንጅት እንሰራለን ብለዋል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ኢትዮ ቴሌኮም የዲጂታል ኢትዮጵያን ጉዞ ለማሳካት ያከናወናቸውን በተለይም ገጠራማ አካባቢዎችን ጨምሮ ለዜጎች የዲጂታል መሠረተ ልማት ተደራሽ ለማድረግ እንዲሁም በቴሌብር ዲጂታል መፍትሔዎች፣ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች እና ማኅበራዊ ኃላፊነት ስላከናወናቸው ተግባራት ገልጸዋል፡፡
የስማርት ሲቲ ፕሮጀክትን ጨምሮ እንደ ግብርና፣ ትምህርት፣ ጤና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ትራንስፖርት፣ ፋይናንስ እና ቱሪዝም ያሉ ዘርፎችን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል ግዙፍ አቅም መገንባቱንም አረጋግጠዋል፡፡
በመጨረሻም ተቋማቱ የዲጂታል ኢትዮጵያ ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠን ቋሚ የጋራ መድረክ በመፍጠር የዜጎችን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ንግድና ኢንቨስትመንት ስኬት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ ውጤት ማሳያ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ...
Mar 27, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ አህጉራዊ የኢንቨስትመንት ማዕከልነትን እያረጋገጠ ...
Mar 26, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025