🔇Unmute
ድሬደዋ፤ መጋቢት 24/2018(ኢዜአ)፦ በለውጡ አመታት በድሬደዋ አስተዳደር የተከናወኑ የልማትና ሰላም ተግባራት ውጤት መመዝገባቸውን በብልፅግና ፓርቲ የድሬደዋ አስተዳደር ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ተናገሩ።
የድሬደዋ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በለውጡ አመታት የተሰሩ የልማትና ሰላም ጉዳዮች ላይ ዛሬ ተወያይተዋል።

ውይይቱን የመሩት በብልጽግና ፓርቲ የድሬደዋ አስተዳደር ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በወቅቱ፤ የለውጡ አመራር ህዝብን በማሳተፍ ሀገርንና ድሬደዋን የሚያሻግሩ ተጨባጭ ልማትን አስመዝግቧል ብለዋል።
በለውጡ አመታት በመደመር እሳቤ የተከናወኑ በፖለቲካዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ውጤት መምጣቱንም አስረድተዋል።
በድሬደዋ ገጠርና ከተማ የተተገበሩ የልማት ተግባራት ከተረጂነት ወደ አምራችነት እያሸጋገሩና ድህነትን በተጨባጭ እየቀነሱ እንደሚገኙም አንስተዋል።
በተለይም በከተማ በአምራች ኢንዱስትሪው፣ በኮሪደር ልማት፣ በቱሪዝም፣ በስራ ዕድል ፈጠራ የተሰሩ ስራዎች የህዝብን ተጠቃሚነት በተጨባጭ ያረጋገጡ መሆናቸውን በመግለፅ።
በገጠር ቀበሌዎችም የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃን በተቀናጀ መንገድ በማከናወን ለግብርና ምርትና ምርታማነት መጎልበት መሠረታዊ መደላድል የፈጠሩ ተጨባጭ ለውጦች መመዝገባቸውን አስታውቀዋል።

ይህን ምቹ መደላድል በመጠቀም የአነስተኛ መስኖና የመጠጥ ውሃ በማስፋፋት፣ በአረንጓዴ አሻራ የፍራፍሬ ምርትን በላቀ ደረጃ በማጎልበት፣ በሌማት ትሩፋት የእንሰሳት ምርታማነትን በመጨመር ማህበረሰቡን ከተረጂነት ወደ አምራችነት የማሸጋገሩ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ከፍተኛ አመራሮች በበኩላቸው ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በድሬደዋ ገጠርና ከተማ የተከናወኑ የሰላም፣ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ስራዎች የህዝብን ተጠቃሚነት በተጨባጭ እያረጋገጡ መሆናቸውን አንስተዋል።
በስምንቱ የለውጥ አመታት የተከናወኑ ሁለንተናዊ ልማቶች ድሬደዋ የብልጽግና ትልሞች የተሳካባት ቀዳሚ አካባቢ እንድትሆን አስቻይ ወረቶች የተፈጠረባት መሆኑንም ጠቅሰዋል።
የተጀመሩትን አበረታች ውጤቶችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሻገር የተቀናጀ ርብርብ እንደሚያደርጉም አመራሮቹ አረጋግጠዋል።
ሀዋሳ ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡-በሲዳማ ክልል ዘመናዊና ቀልጣፋ አሰራሮችን በመዘርጋት በርካታ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ወደ ክልሉ በመሳብ የዜጎችን ተጠቃ...
Apr 23, 2026
ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 9/2018 (ኢዜአ)፦ በሀገራዊ ለውጡ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የተሰጠው ትኩረት በአስተዳደሩ የአምራች ኢንዱስትሪዎች ተኪና ወጪ ምርቶችን የማምረ...
Apr 17, 2026
ጅግጅጋ፣መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፡- መንግሥት የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ተመለከተ። የኢትዮጵያ ከተሞች የ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር አህጉራዊ የልማት አጀንዳ ...
Mar 26, 2026