
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን (ዶ/ር) ገለጹ።
ዩኒቨርሲቲው ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳተፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው "የአባይ ዘመን ትውልድ" በሚል መሪ የኪነ ጥበብ መድረክ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል።

በመድረኩ የግድቡን ሁለንተናዊ ጠቀሜታና ቀጣናዊ ትስስር የሚያወሱ የስነ ጽሁፍና ሙዚቃ ስራዎች ቀርበዋል።
የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለፁት ግድቡ መላው ኢትዮጵያዊያን አሻራቸውን ያሳረፉበትና የትውልዱ ኩራት ነው።
በትውልድ ቅብብሎሽ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ለሚገኘው ሕዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
ዩኒቨርሲቲው ግድቡ ለተፋሰሱ አገራት የሚሰጠውን ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ማህበረሰቡ እንዲገነዘብ ለማድረግ የጥናትና የምርምር ማዕከል ለመክፈት በዝግጅት ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የህዳሴ ግድብ ከኤሌክትሪክ ኃይል በተጨማሪ ለወደፊቱም ቱሪዝምን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎችን እንደሚያስገኝ ገልጸዋል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ አቶ ጌታቸው ፊሊጾስ በበኩላቸው ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ መሰረት የሚጥል ግዙፍ ፕሮጀክት መሆኑን ገልፀዋል።
ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የተለያዩ የገቢ ማሰባሰብያ ፕሮግሞችን በማዘጋጀት ዜጎች ግዴታቸውን እንዲወጡ እየተደረገ እንደሚገኝ የተናገሩት ደግሞ የክልሉ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር አቶ ለሜሳ ኔኖ ናቸው ።
ጅግጅጋ፣መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፡- መንግሥት የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ተመለከተ። የኢትዮጵያ ከተሞች የ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር አህጉራዊ የልማት አጀንዳ ...
Mar 26, 2026
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025