🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018(ኢዜአ) ፦ኢትዮጵያ እና የእስያ መሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ በመሰረተ ልማት ግንባታ ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆናቸውን አስታወቁ።
የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ከእስያ መሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የኮርፖሬት ፀሐፊ ሰር ሼራርድ ካውፐር-ኮልስ ጋር በቤጂንግ ተወያይተዋል።
ውይይቱ በኢትዮጵያ እና በባንኩ መካከል ያለውን አጋርነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ነው።
በውይይቱ ወቅት በዋናነት በትብብር ሊከናወኑ የሚችሉ እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው የመሰረተ ልማት አውታሮችና የልማት ውጥኖች ላይ የሀሳብ ልውውጥ ተደርጓል።
የእስያ መሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ለቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ሊያደርግ በሚችለው የፋይናንስ ድጋፍ ዙሪያም ሰፊ ምክክር ተካሂዷል።
የገንዘብ ሚኒስትሩ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን የአቪዬሽን ማዕከልነት ለማጠናከር እና ለሀገሪቱ የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ ዕድገት ያለውን ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ አስረድተዋል።
ሁለቱ ወገኖች የግል ዘርፍ ፋይናንስን በማንቀሳቀስ ረገድ ያለውን ትብብር ለማሳደግ በሚቻልባቸው ዕድሎች ላይም ተወያይተዋል።
ሚኒስትሩ ባንኩ የግል ኢንቨስትመንትን በማበረታታት እና የግል ባለሀብቶች በመሠረተ ልማት ዘርፎች ላይ የጎላ ተሳትፎ እንዲኖራቸው በማድረግ ረገድ ያለውን ሚና አጽንኦት ሰጥተው አንስተዋል።
ሁለቱም ወገኖች በኢትዮጵያ ዘላቂ መሠረተ ልማትን ለማስፋትና በግሉ ዘርፍ የሚመራ የኢኮኖሚ እድገትን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ መግለጻቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል።
ሀዋሳ ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡-በሲዳማ ክልል ዘመናዊና ቀልጣፋ አሰራሮችን በመዘርጋት በርካታ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ወደ ክልሉ በመሳብ የዜጎችን ተጠቃ...
Apr 23, 2026
ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 9/2018 (ኢዜአ)፦ በሀገራዊ ለውጡ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የተሰጠው ትኩረት በአስተዳደሩ የአምራች ኢንዱስትሪዎች ተኪና ወጪ ምርቶችን የማምረ...
Apr 17, 2026
ጅግጅጋ፣መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፡- መንግሥት የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ተመለከተ። የኢትዮጵያ ከተሞች የ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር አህጉራዊ የልማት አጀንዳ ...
Mar 26, 2026