የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በነዳጅ አቅርቦት ዙሪያ በሚፈጸሙ ወንጀሎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ቀጥሏል

Mar 23, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 12/2018(ኢዜአ) ፦ በነዳጅ አቅርቦት ዙሪያ በሚፈጸሙ ወንጀሎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

በነዳጅ ስርጭትና ግብይት ሂደት ላይ የሚታዩ ሕገ-ወጥ ተግባራትን ለመቆጣጠር በስድስት ክልሎችና በሁለት የከተማ አስተዳደሮች የተጀመረው የተቀናጀ ዘመቻ መጠነ ሰፊ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገልጸዋል።


ባለፉት ቀናት በተደረገው ከፍተኛ ክትትልና ቁጥጥርም የተለያዩ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ኢዜአ ከሚኒስቴሩ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በዚህ መሰረትም በሕገ-ወጥ መልኩ ሲዘዋወር የነበረ 250 ሺህ 221 ሊትር ቤንዚን እና 198 ሺህ 432 ሊትር ናፍጣ ተይዞ መወረሱን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ከተወረሰው ነዳጅ መካከል በሽያጭ ለጥቅም እንዲውል ከተደረገው ውስጥ ከ48 ሚሊዮን 663 ሺህ ብር በላይ ለመንግሥት ገቢ መሆኑን ሚኒስትሩ የገለጹ ሲሆን በአሻጥሩ ተሳትፈው የተገኙ 613 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስረድተዋል።

ከተያዙት ግለሰቦች መካከል የንግድ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች፣ የቡድን መሪዎች፣ የሬጉላቶሪ ባለሙያዎች፣ የነዳጅ ማደያ ባለቤቶችና ሠራተኞች እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ የጸጥታ አካላት እንደሚገኙበት ጠቁመዋል።


እርምጃው በታችኛው መዋቅር ላይ ብቻ ሳይሆን በውሳኔ ሰጪዎች ላይም ያነጣጠረ መሆኑን ገልጸው ይህ የተቀናጀ የቁጥጥር ሥራ በዘርፉ የሚታየውን አሻጥር በመቅረፍ ፍትሃዊ የነዳጅ ስርጭት እንዲኖር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

ያለውን ዓለም አቀፋዊ የነዳጅ ገበያ ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ነዳጅ አከፋፋዮችና ህብረተሰቡ ነዳጅን በቁጠባና በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት እንዲጠቀሙም ሚኒስትሩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

Ethiopian News Agency #ኢዜአ #ነዳጅ

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቷል

ጅግጅጋ፣መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፡- መንግሥት የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ተመለከተ። የኢትዮጵያ ከተሞች የ...

Apr 1, 2026

የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር የልማት አጀንዳ ነው

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር አህጉራዊ የልማት አጀንዳ ...

Mar 26, 2026

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025