የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

ማምሻውን በቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ እጅግ ዘመናዊ ሆኖ የተገነባውን የድል ፕላዛ እና የቁርጡሚ የወንዝ ዳርቻ ልማትን አጠናቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Mar 11, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ የካቲት 30/2018(ኢዜአ)፦ማምሻውን በቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ እጅግ ዘመናዊ ሆኖ የተገነባውን የድል ፕላዛ እና የቁርጡሚ የወንዝ ዳርቻ ልማትን አጠናቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

በአንድ ወቅት የወንጀለኞች መሸሸጊያና የቆሻሻ መጣያ የነበረውን ስፍራ፤ ዛሬ ውብ፣ ለአይን ማራኪ እና የከተማችን አንዱ የቱሪስት መስህብ አድርገን ገንብተነዋል ሲሉም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል።


የድል ፕላዛ እና ቁርጡሚ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፦

- 21,906 ካሬ ሜትር የወለል ስፋት ያለው ፕላዛ፣

- በአንድ ጊዜ 500 መኪናዎችን ማቆም የሚችሉ ባለ ሦስት ወለል የመሬት ውስጥ ወለሎችን (Basements parking) መኪና ማቆሚያን አካትቷል።

- ዘመናዊ የፓርኪንግ ማኔጅመንት ሲስተም፣ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያ እና የእሳት አደጋ መከላከያ ዘዴ የተገጠመለትም ነው።

- 7 ሄክታር መሬት የሚሸፍን ውብ የአረንጓዴ ስፍራ፣ ምቹ የእግረኛ መንገዶች፣ ዘመናዊና ባህላዊ የስጦታ ዕቃ መሸጫዎች፣ ሬስቶራንቶች፣ ካፌዎች እና ቢሮዎችንም ይዟል።

- በተያያዘም 2.2 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የቁርጥሜ የወንዝ ዳርቻ ልማት፤

- የተለያዩ የሕዝብ አገልግሎት መስጫዎችን፣ የሕፃናት የአዋቂዎች ስፖርት ማዘውተሪያዎችን አካትቶ በጽዱና በቆንጆ ሁኔታ ተገንብቷል።


- የህፃናት መጫወቻ

- ⁠የስፓርት ሜዳ

- ⁠5 አንፊ ትያትር አካትቷል።

ስለ ከተሜነት ስናወራ የተሳለጠ መሰረተ ልማት ያለዉ ፣የህዝብ የጋራ መገልገያ ስፍራዎች ያሉት፣ የስራ እድልን የሚፈጥር ንፁህ፣ ውብ፣ምቹ መኖሪያ እና ጤናማ አካባቢን መፍጠር ነው ሲሉም ገልጸዋል።

ይህ ፕሮጀክት በተቀመጠለት ጊዜና በታለመለት የጥራት ደረጃ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ ላደረጋችሁ ወጣት የምህንድስና እና የአርክቴክቸር ባለሙያዎች፣ የዲዛይንና ግንባታ ቢሮ፣ የአረንጓዴና ውበት ቢሮ፣ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን፣ የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ድርጅት፣ ቲ ኤን ቲ (TNT) ኮንስትራክሽን፣ እንዲሁም በየደረጃው ለነበራችሁ ባለሙያዎችና የጉልበት ሠራተኞች በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቷል

ጅግጅጋ፣መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፡- መንግሥት የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ተመለከተ። የኢትዮጵያ ከተሞች የ...

Apr 1, 2026

የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር የልማት አጀንዳ ነው

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር አህጉራዊ የልማት አጀንዳ ...

Mar 26, 2026

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025