🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ታኅሣስ 30/2018 (ኢዜአ)፡- ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባለፉት ሥድስት ወራት 10 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ የተለያዩ ፕሮጀክቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሰጠ።
የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አባስ መሐመድ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት÷ ፈቃድ የተሰጣቸው 146 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ናቸው።
ከእነዚህ ፕሮጀክቶች መካከል 26ቱ 1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ያስመዘገቡ የዳያስፖራ ባለሃብቶች መሆናቸውን ተናግረዋል።
በአጠቃላይ ፈቃድ የተሰጠባቸው ዘርፎችም ግብርና፣ አገልግሎት እና ኢንዱስትሪ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ፕሮጀክቶቹ ወደ ሥራ ሲገቡ ለ21 ሺህ 679 ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጠር ይጠበቃል ብለዋል።
በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ ፈቃድ ያወጡ ፕሮጀክቶች ያስመዘገቡት ካፒታል ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ2 ነጥብ 95 ቢሊየን ብር ብልጫ ማሳየቱንም ጠቅሰዋል።
በሌላ በኩል የተረከቡትን መሬት በአግባቡ ባላለሙ 40 ፕሮጀክቶች ላይ የተለያየ ደረጃ ያለው ርምጃ መወሰዱን አስረድተዋል።
በዚህም መሠረት 33 ማስጠንቀቂያ እንዲሁም ሰባት ፕሮጀክቶች ላይ ደግሞ ውልና የኢንቨስትመንት ፈቃድ የመሰረዝ ርምጃ መወሰዱን ነው ያስረዱት።
ጅግጅጋ፣መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፡- መንግሥት የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ተመለከተ። የኢትዮጵያ ከተሞች የ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር አህጉራዊ የልማት አጀንዳ ...
Mar 26, 2026
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025