🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ህዳር 3/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በኢትዮጵያ የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎት እንዲሰጡ የተፈቀደላቸውን የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶችን ስም ዝርዝር ለሕዝቡ ይፋ አድርጓል።
ባንኩ ለኢዜአ በላከው መግለጫ መሰረት ፣ ቀደም ሲል የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎት እንዳይሰጥ ታግዶ የነበረውና ዋና መስሪያ ቤቱ በአሜሪካ ቪርጂኒያ ግዛት በፎልስ ቸርች የሚገኘው ራማዳ ፔይ (ካህ) በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ አጠቃላይ ግምገማ ከተካሄደ በኋላ በሕጋዊ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች ስም ዝርዝር ውስጥ ዳግም እንዲካተት መደረጉን ባንኩ በመግለጫው አመልክቷል።
ከዚህ ውሳኔ ላይ ሊደረስ የቻለው በሀገሪቱ ሕግና ደንብ መሠረት በድርጅቱ ላይ አስፈላጊው የቁጥጥርና የክትትል ሂደት ከተጠናቀቀ በኋላ መሆኑን ገልጿል።
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ አገልግሎት እንዳይሰጡ ታግደው የሚገኙ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች በሙሉ የሀገሪቱ ሕግና ደንብ የሚጠይቀውን መስፈርት ለማሟላት አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ አሳስቧል።
የብሔራዊ ባንክ ዓላማ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች በግልጽነትና ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት ብቻ እንዲሠሩ ድጋፍ ማድረግ እንደሆነ ነው ያስታወቀው።
በውጭ አገር የሚኖሩ ሰዎች ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ በሚያስተላልፉበት በማንኛውም ወቅት ሕጋዊና ግልጽ የሆነ አካሄድ መከተላቸውን ማረጋገጥ እንደሚኖርባቸው አስገንዝቧል።
ሕጋዊ ፈቃድ በተሰጣቸው የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች በኩል ገንዘብ መላክ ገንዘቡ ደህንነቱ ተጠብቆና ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርንና አሸባሪነትን በገንዘብ መደገፍን የሚጻረረውን አሠራር ተከትሎ ወደ ተቀባዩ እንዲደርስ እንደሚያደርግ ነው በመግለጫው ያመለከተው።
ሕዝቡ ፈቃድ የተሰጣቸው የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶችን ለይቶ ለማወቅ ይችል ዘንድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሕጋዊ ድርጅቶችን ስም ዝርዝር በድረ ገጹhttps://nbe.gov.et/mta/ ይፋ ማድረጉን ባንኩ ጠቁሟል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሕጋዊ የሐዋላ አገልግሎትን ለማበረታታትና የፋይናንስ ዘርፍን ጤናማ ዕድገት ለመደገፍ የሚረዳ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ግልጽና ቀልጣፋ የፋይናንስ ምህዳር እንዲኖር በትጋት መሥራቱን እንደሚቀጥል አስታውቋል።
ጅግጅጋ፣መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፡- መንግሥት የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ተመለከተ። የኢትዮጵያ ከተሞች የ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር አህጉራዊ የልማት አጀንዳ ...
Mar 26, 2026
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025