የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

አርሶ አደሩ ቀድሞ የደረሰን ሰብል ፈጥኖ በመሰብሰብ ወቅቱን ካልጠበቀ ዝናብ ከወዲሁ መከላከል ይጠበቅበታል

Nov 13, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

ደሴ ፤ ህዳር 3/2018(ኢዜአ)፦አርሶ አደሩ ቀድሞ የደረሰን ሰብል ፈጥኖ በመሰብሰብ ወቅቱን ካልጠበቀ ዝናብ ከወዲሁ መከላከል እንደሚጠበቅበት በኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የምስራቅ አማራ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል አሳሰበ።

በማዕከሉ የትንበያና ቅደመ ማስጠንቀቂያ ዴስክ ኃላፊ ሉባባ መሀመድ፤ ወቅቱ ደረቅ፣ ፀሐያማና ነፋሻማ ቢሆንም ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እንደሚከሰት ትንበያዎች ያመለክታሉ ሲሉ ለኢዜአ ተናግረዋል።


ትንበያውን በመከተልም አርሶ አደሩ የደረሰ ሰበልን ፈጥኖ በመሰብሰብ ወቅቱን ካልጠበቀ ዝናብ ከወዲሁ እንዲከላከል አሳስበዋል።

የማዕከሉ የልማት ሚቲዎሮሎጂ ዴስክ ኃላፊ አቶ እንዳላማው ወንዴ በበኩላቸው፤ ከጥቅምት እስከ ጥር ባሉ የበጋ ወራት ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይጠበቃል ብለዋል።


አርሶ አደሩ የደረሰ ሰብል ከመሰብሰብ ጎን ለጎን ጎርፍን በዳር በማቆር ለመስኖ፣ ለቋሚ ተክልና ለእንስሳት ግጦሽ ልማት እንዲጠቀም መክረዋል።

በሌላ በኩል ጠዋትና ማታ ደግሞ ከፍተኛ ቅዝቃዜና ውርጭ ሊከሰት ስለሚችል ሕብረተሰቡ አለባበሱንና አመጋገቡን በማስተካከል እራሱን ከጉዳት እንዲጠብቅም መልዕክት አስተላልፈዋል።

በደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ የሰብል ልማት ቡድን መሪ አቶ ይመር ሰይድ ፤ በዞኑ ቀድሞ የደረሰ ሰብል በወቅቱ እንዲሰበሰብ የተጠናከረ የባለሙያ ድጋፍ እየተደረገ ነው ብለዋል።


በዚህም እስካሁን በ32 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የለማ ጤፍ፣ ማሽላ፣ በቆሎ፣ ማሾና የጥራጥሬ ሰብል መሰብሰቡን አስታውቀዋል።

የሰብል መሰብሰብ ስራውን በአርሶ አደሩና በበጎፈቃደኞች ትብብር አጠናክሮ በማስቀጠል እስከ ታህሳስ አጋማሽ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ገለጸዋል።


አርሶ አደሩ የሰበሰበውን ሰብል በጥንቃቄ እንዲከምርና በንፁህ አውድማ በመውቃት ለምርት ጥራት ትኩረት እንዲሰጥም መክረዋል።

በደቡብ ወሎ ዞን አጠቃላይ በመኸር ከለማው 432 ሺህ ሄክታር መሬት ከ15 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ ከግብርና መምሪያው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቷል

ጅግጅጋ፣መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፡- መንግሥት የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ተመለከተ። የኢትዮጵያ ከተሞች የ...

Apr 1, 2026

የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር የልማት አጀንዳ ነው

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር አህጉራዊ የልማት አጀንዳ ...

Mar 26, 2026

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025