🔇Unmute
ነቀምቴ ፤ ጥቅምት 6/2018 (ኢዜአ) ፡- በምሥራቅ ወለጋ ዞን በበጋ መስኖ የሚካሄድ የስንዴ ልማት ተጠናክሮ መቀጠሉን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ገለጸ።
በዞኑ ጉቶ ጊዳ ወረዳ ጋሪ ቀበሌ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሂዷል።
በዚህ ወቅት የምሥራቅ ወለጋ ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት ምክትል ሀላፊ ዶክተር ደረጄ ብርሃኑ እንደተናገሩት፤ በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ሂደት ውስጥ የግብርናው ዘርፍ ጉልህ ድርሻ አለው።

በዞኑ ባለፉት ዓመታት በበጋ መስኖ የስንዴ ልማት ላይ የተገኘውን ውጤት መሰረት በማድረግ በቀጣይ በተሻለ መልኩ አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።
በዘንድሮ የበጋ ወቅትም የስንዴ ልማቱን አጠናክሮ ለማስቀጠል አርሶ አደሮችን በመደገፍ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረው፤ ለአርሶ አደሮቹ የግብዓት አቅርቦት ማመቻትን ጨምሮ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ ነው ብለዋል።
የጉቶ ጊዳ ወረዳ የግብርና ጽህፈት ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ ገረመው አስፋው በበኩላቸው፤ በወረዳው በኩታ ገጠም በመስኖ ስንዴን ለማምረት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በወረዳው በጋሪ ቀበሌ መልካ ዶሪ ክላስተር ጨምሮ 15 ሄክታር መሬት ላይ ልማቱ እየተካሄደ ነው ብለዋል።
ከአካባቢው አርሶ አደሮች መካከል ታሪኩ ስጦታው በሰጡት አስተያየት፤ አምና በግማሽ ሄክታር መሬት ስንዴን በመስኖ በማልማት አስር ኩንታል ምርት ማግኘታቸውን በማስታወስ ዘንድሮም ተግባሩን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
ጅግጅጋ፣መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፡- መንግሥት የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ተመለከተ። የኢትዮጵያ ከተሞች የ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር አህጉራዊ የልማት አጀንዳ ...
Mar 26, 2026
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025