🔇Unmute
ድሬዳዋ፤ ጥቅምት 4/2018(ኢዜአ)፦ ጀግናው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ በድሬዳዋ ኢንቨስት ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገለጸ።
አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ከአስተዳደሩ ከንቲባ እና ሌሎችም አመራሮች ጋር በመሆን የድሬዳዋን የኢንቨስትመንት አማራጮችና መሠረተ ልማት ስራዎች ተዘዋውሮ ተመልክቷል።

ከጉብኝቱም በኋላ ከከንቲባ ከድር ጁሃር እና ካቢኔያቸው ጋር የተወያየ ሲሆን የድሬዳዋን መሠረተ ልማት አቅርቦትና የልማት አማራጮች አድንቋል።
የነፃ ንግድ ቀጣና፣ የደረቅ ወደብ እና የኮንቬንሽን ማዕከል ኢንቨስትመንት ለመጀመር ሳቢ መሆናቸውን በማንሳት ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎትና ዝግጁነት ያለው መሆኑን አረጋግጧል።
በከተማዋ እየተከናወነ ያለው የልማት እንቅስቃሴ ከተማዋን የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማእከል ለማድረግ የሚያስችል እንዲሁም በሆቴልና መስተንግዶ ዘርፍ ኢንቨስት ለማድረግ አመቺ ነው ሲልም አክሏል።

ድሬዳዋን የንግድ፣ የኢንዱስትሪ እና የቱሪዝም ኮንፈረንስ ከተማ ለማድረግ በከተማው የተጀመሩ ስራዎች ኢንቨስት ለማድረግ ስለሚያመቹ ሌሎች ባለሃብቶችም በዘርፉ እንዲሰማሩ ምክረ ሀሳቡን አጋርቷል።
ከተማዋ በጎብኚዎች ተመራጭ የሚያደርጋት የአየር ንብረት እና የተፈጥሮ ጸጋን የታደለች መሆኗን ገልፆ ይህም ለሆቴል ኢንቨስትመንቱ መሳካት ተጨማሪ አቅም እንደሚሆንም አመልክቷል።
ጅግጅጋ፣መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፡- መንግሥት የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ተመለከተ። የኢትዮጵያ ከተሞች የ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር አህጉራዊ የልማት አጀንዳ ...
Mar 26, 2026
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025