🔇Unmute
አዲስ አበባ፤መስከረም 29/2018(ኢዜአ)፦ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የጋራ ተጠቃሚነትን እውን ከማድረግ ባሻገር ሜጋ ፕሮጀክቶችን በራስ አቅም ሰርቶ ማጠናቀቅ እንደሚቻል ያረጋገጥንበት ነው ሲሉ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አመራር አባላት ገለጹ።
የኢንስቲትዩት አመራር አባላት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጎብኝተዋል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ከበደ ቶሎሳ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ታላቁ የህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያንን የብዙ ዘመን ምኞት እውን ያደረገ ፕሮጀክት ነው።
ታላቁ ህዳሴ ግድብ መላው ኢትዮጵያውያንን ወደ ብርሀን ያመጣ የድል ብስራት መሆኑን ጠቁመው፤ አገሪቷ ከድህነት የምትወጣበትን አቅጣጫ ያሳየ ታላቅ ፕሮጀክት መሆኑን ጠቁመዋል።
ኢንስቲትዩቱ ለግድቡ በተለያዩ መንገዶች የቴክኖሎጂ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጸው፤ ዲጂታላይዜሽንን ለማረጋገጥ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው አመልክተዋል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የሰው ሀብት ልማት እና አስተዳደር ዳይሬክተር ግርማቸው ጌቱ በበኩላቸው፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ የያዘቻቸውን ስትራቴጂያዊ ግቦች የሚያሳካ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል።
እንዲሁም በራስ አቅም መልማት እና ማደግ እንደሚቻል ትምህርት የሰጠ ፕሮጀክት መሆኑን ጠቁመዋል።
ታላቁ ህዳሴ ግድቡ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ትልቅ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸው፤ በቀጣይም ሌሎች ፕሮጀክቶችን በራስ አቅም ማጠናቀቅ እንደሚቻል ያስተማረ መሆኑን ተናግረዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የጋራ ተጠቃሚነትን እውን ከማድረግ ባሻገር ሜጋ ፕሮጀክቶችን በራስ አቅም ሰርቶ ማጠናቀቅ እንደሚቻል የታየበት መሆኑን ገልጸዋል።
አብዛኛው ቴክኖሎጂ የኤሌክትሪክ ሀይል እንደሚፈልግ ገልጸው፤ ቀጣይ በመንግስት የተያዙ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ከመደገፍ አኳያም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።
ጅግጅጋ፣መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፡- መንግሥት የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ተመለከተ። የኢትዮጵያ ከተሞች የ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር አህጉራዊ የልማት አጀንዳ ...
Mar 26, 2026
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025