ባሕርዳር፤ ሐምሌ 22/2017(ኢዜአ)፡- የአማራ ክልል ምክር ቤት 10ኛ መደበኛ ጉባኤ በ2018 በጀት ዓመት ለሚከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ማስፈፀሚያ ከ225 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አፀደቀ።
የክልሉ ገንዘብ ቢሮ ሃላፊ ጥላሁን መሀሪ(ዶ/ር) ረቂቅ በጀቱን ለምክር ቤቱ ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት፤ በጀቱ የክልሉን የመልማት ፍላጎት መሰረት ያደረገ ነው።
በጀቱ የ2018 በጀት ዓመትና የ5 ዓመት የመካከለኛ ዘመን የልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅድ ሰራዎችን ታሳቢ የተደረገ ነው ብለዋል።
ወቅታዊ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ፣ የሪፎርም ስራዎችንና ሌሎች የትኩረት መስኮችን በጀቱ እንደሚያካተት ጠቅሰው፤ ከ2017 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ49 ነጥብ 6 በመቶ ብልጫ እንዳለው አስረድተዋል።
በጀቱ የሚሸፈነው በክልሉ የተለያየ የገቢ፣ ከፌዴራል መንግስትና ከሌሎች ምንጮች እንደሆነም ጠቅሰዋል።
በጀቱ በትክክል የህዝብን የመልማት ፍላጎት መሰረት በማድረግ በቁጠባ ጥቅም ላይ እንዲውል ተገቢው ክትትል፣ ቁጥጥርና ድጋፍ እንደሚደረግ ተመልክቷል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ፤ በጀቱ በፍትሃዊነት የተደለደለ በመሆኑ የህዝብን የልማት ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ አግባብ በቁጠባ ጥቅም ላይ እንዲውል የሚደረግ መሆኑን ገልጸዋል።
በየደረጃው ያለው አመራር ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በመሰብሰብ የህዝብን የልማት ፍላጎት በአቅም ልክ ማከናወን ይገባል ብለዋል።
በዚህ በጀት ዓመት 25ቢሊዮን ብር ከህብረተሰብ ተሳትፎ በገንዘብ ለመሰብሰብ መታቀዱን ጠቅሰው፤ ይህ እንዲሳካ መረባረብ እንደሚገባ አመልክተዋል።
የምክር ቤቱ 10ኛ መደበኛ ጉባዔ የቀረበውን ረቂቅ በጀትና የ2017 በጀት ዓመት 13 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት መርምሮ አፅድቋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025