ጅማ፤ ሐምሌ 22/2017(ኢዜአ)፡- ተኪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የማምረት ተግባርን በማጠናከር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ውጤታማ ስራ መሰራቱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍስሀ ይታገሱ(ዶ/ር) ገለጹ።
ኮርፖሬሽኑ በሀገሪቱ የሚያስተዳድራቸውን የልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ተወካዮች ያሳተፈ የስራ አፈጻጸም ግምገማ በጅማ እያካሄደ ነው።
በመድረኩ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍስሀ ይታገሱ(ዶ/ር) የተጠናቀቀው በጀት ዓመት የኮርፖሬሽኑ አፈጻጸም የእቅዱን 99 በመቶ መሆኑን ገልጸዋል።
በበጀት ዓመቱ ምርቶችን በሀገር ውስጥ እንዲመረቱ ከማድረግ አንጻር 18 ቢሊዮን ብር የሚገመት ምርት በ11 የኢኮኖሚ ዞኖችና በሁለት ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ መመረቱን ገልጸዋል።
6 ቢሊዮን ብር የገበያ ትስስር ለመፍጠር ታቅዶ 14 ቢሊዮን ብር የገበያ ትስስር በመፍጠር አበረታች እንቅስቃሴ መደረጉንም አነሰተዋል።
ከ80ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች የስራ እድል የተፈጠረ ሲሆን፤ 206 ባለሀብቶች በተለያዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ተሳትፈዋል ብለዋል።
ኮርፖሬሽኑ 11 ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ሁለት የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በማስተዳደር የኢንዱስትሪ ልማት ስራዎችን እየሰራ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።
በጅማ የሚገኘውን የኢንዱስትሪ ፓርክ ሁለት አቮካዶ ምርት ላይ የሚሰሩ ካምፓኒዎችና አራት ደግሞ በቡና ፕሮሰሲንግ ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች ውል ፈጽመው ማሽነሪዎችን በማስገባት ላይ እንደሚገኙም ተናግረዋል።
በተለይም የጅማ ከተማ የኮሪደር ልማቱ ለኢንዱስትሪ ዘርፍ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ጠቅሰው፤ አሁን ላይ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ከፍተኛ የልማት ፍላጎቶች እየታዩ ነው ብለዋል።
የቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ስራ አስኪያጅ አቶ ትንሳኤ ይማም በበኩላቸው፤ 24 ሼዶች ተገንብተው ስራ መጀመራቸውን ገልጸዋል።
ከ29ሺህ ለሚበልጡ ሰዎች የስራ ዕድል መፍጠር ተችሏል ሲሉም አስታውቀዋል።
የአዳማ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ስራ አስኪያጅ አቶ ጉልላት አበበ፤ በልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ የተለያዩ የኢንዱስትሪ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አመልከተው፤ 19 ሼዶች ሲኖሩ፤ 13 ባለሀብቶች መሳተፋቸውን አንስተዋል።
በጋርመንትና ቴክስታይል፣ በኤሌክትሮ መካኒካል እና የመሳሰሉ ስራዎች እየተከናወኑ መሆነን ገልጸው፤ የተለያዩ ምርቶችም ወደ ውጭ እየላኩ መሆኑን ተናግረዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025