ሀዋሳ፤ ሐምሌ 22/2017 (ኢዜአ)፡-በሲዳማ ክልል በስምንት ከተሞች የኮሪደር ልማት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡
በክልሉ የተለያዩ ከተሞች ያሉ ነዋሪዎች በበኩላቸው የኮሪደር ልማት ሥራው ከተሞችን ምቹና ተመራጭ ከማድረግ ባለፈ ለዜጎች የሥራ ዕድል ፈጠራ እያገለገሉ በመሆኑ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የበኩላቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
የቢሮ ሃላፊው አቶ አሻግሬ ጀምበሬ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ እንደሀገር የተጀመረው የኮሪደር ልማት ከተሞችን ለነዋሪዎችና ለኢንቨስትመነት ተመራጭ እያደረገና ዕድገታቸውን እያፋጠነ ነው፡፡
በአሁኑ ወቅትም በሲዳማ ክልል በስምንት የተለያዩ ከተሞች ከ28 ኪሎ ሜትር በላይ የሚሸፍን የኮሪደር ልማት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በዚህም ሀዋሳን ጨምሮ ይርጋለም፣ ወንዶገነት፣ ዳዬ፣ አለታ ጩኮ፣ አለታ ወንዶ፣ ለኩና ይርባ ከተሞች የኮሪደር ልማት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አቶ አሻግሬ ገልጸዋል፡፡
በሀዋሳ ከተማ ብቻ ከ20 ኪሎ ሜትር በላይ የኮሪደር ልማት ሥራ በሁለት ምዕራፎች ተከፍሎ እየተከናወነ መሆኑን የገለጹት አቶ አሻግሬ፣ የኮሪደር አካል የሆነው ከስምንት ኪሎ ሜትር በላይ የአስፓልት መንገድ ግንባታም እየተፋጠነ መሆኑን አስረድተዋል።
በከተሞቹ የኮሪደር ልማት ሥራው እየተፋጠነ መሆኑን የገለጹት ሃላፊው፣ ሥራውን በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ግብ ተይዞ እየተሰራ መሆኑንም አመልክተዋል።
የኮሪደር ልማቱ የከተሞችን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን በማሳለጥና ማህበራዊ ችግሮችን እየፈታ በመሆኑ ህብረተሰቡ በተለያየ መንገድ ተሳትፎውን እያሳደገ መምጣቱን ገልጸዋል።
"የኮሪደር ልማት ሥራው በክልሉ መንግስት ልዩ ትኩረት እየተመራ ነው" ያሉት አቶ አሻግሬ፣ ድጋፍና ክትትልን ጨምሮ ተሞክሮ በመቀመር ስራውን ለማስፋፋት እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።
የኮሪደር ልማቱ ስማርት ሲቲን ለመገንባት የተጀመረውን ጥረት በሚያግዝ መልኩ እየተከናወነ መሆኑንም ገልጸው፣ ለስኬታማነቱ ተቋማት በቅንጅት እንዲሰሩ የሚያስችል አሰራር ተዘርግቷል ብለዋል።
በክልሉ የይርጋለም ከተማ ነዋሪው አቶ ጌታቸው ተፈራ በበኩላቸው ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ለከተሞች በተሰጠው ልዩ ትኩረት በከተማቸውም የኮሪደር ልማት ሥራ እየተከናወነ መሆኑንና ገጽታዋም እየተቀየረ መሆኑን ገልጸዋል።
ከተማዋ ረዥም እድሜን ብታስቆጥርም የእድሜዋን ያህል በልማት እንዳልገፋች አስታውሰው በከተማው እየተከናወነ ባለው የልማት ሥራ መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡
በወንዶገነት ከተማ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ እየተከናወነ ያለው የመሰረተ ልማት ሥራ ተጠቃሚ እያደረጋቸው መሆኑን የገለጹት ደግሞ የከተማዋ ነዋሪ አቶ መሳፍንት በራሶ ናቸው፡፡
የኮሪደር ልማቱ ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ ከማድረግ ባለፈ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ እድል መፍጠሩንም ተናግረዋል፡፡
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025