የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የዓለም ሀገራት ለዘላቂ፣ አካታችና የማይበገር የምግብ ሥርዓት በአንድነት ሊተጉ ይገባል

Jul 30, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ሐምሌ 22/2017 (ኢዜአ)፦የዓለም ሀገራት ለዘላቂ፣ አካታችና የማይበገር የምግብ ሥርዓትን ለመፍጠር የተግባር እርምጃዎችን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሀመድ ገለጹ።

በኢትዮጵያ፣ ጣሊያንና ተመድ አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው ሁለተኛው የምግብ ሥርዓት ጉባኤ ዛሬ ተጠናቋል።

በማጠቃለያ ስነ-ሥርዓቱ ንግግር ያደረጉት የተመድ ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሀመድ፥ ጉባኤው ስኬታማ መሆኑን ጠቅሰው፥ ኢትዮጵያ ላደረገችው የተሟላ መስተንግዶ አመስግነዋል።

እ.አ.አ በ2021 ከተካሄደው የመጀመሪያው የምግብ ሥርዓት ጉባኤ በኋላ የኮቪድ 19፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ እና ሌሎች ፈታኝ ሁኔታዎች ቢኖሩም ከ130 በላይ ሀገራት የተቀናጀ ብሔራዊ የምግብ ሥርዓት ሽግግር ፖሊሲ ቀርጸዋል፤ ወደ ተግባርም የገቡ እንዳሉ አውስተዋል።

ሆኖም ኢ-ፍትሐዊነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ፣ ግጭት፣ የሰብዓዊ ድጋፍ መቀነስ አሁንም ፈተና መደቀናቸውን ጠቅሰው፥ ሞራላዊ እሴቶቻችን ጥያቄ ውስጥ ወድቀዋል ነው ያሉት።

የዘንድሮው ጉባኤ ምን ሰራን፣ ምንስ ይጠበቅብናል፣ የሚለውን የፈተሽንበት ብቻ ሳይሆን የዓለም የምግብ ሥርዓት ንቅናቄ በእርግጥም መኖሩን ያረጋገጥንበት ነው ብለዋል።

ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የምግብ ሥርዓት ለመገንባትም ዓለም አቀፋዊ አንድነትንና የፋይናንስ ትብብር ማደስ፣ ፈጠራ እና አካታችነትን ማጠናከር እንደሚገባም ጠቁመዋል።

አርሶ አደሮችን፣ ሴቶችን፣ ወጣቶችን እና ሥራ ፈጣሪዎችን ያሳተፈ የፖሊሲ እርምጃን ማስፋትም ተገቢ ነው ብለዋል።

ዓለም አቀፍ የልማት ባንኮች፣ ሌሎች የፋይናንስ አመንጪዎች እና የግሉ ዘርፍ ለግብርናው ዘርፍ መጠናከር ኢንቨስት በማድረግ ለምግብ ሥርዓት መሻሻል እንዲሰሩም ጠይቀዋል።

በሀገር በቀል እውቀት የተመሰረተ፣ የአካባቢ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ መስተጋብርን ያገናዘበ የተቀናጀ ተግባርም ወሳኝ ነው ብለዋል።

በአንድነት ስንሰራ ውጤት ማምጣት እንደምንችል ባለፉት አራት ዓመታት ተመልክተናል ያሉት ምክትል ዋና ፀሐፊዋ፥ መንግሥታት ስኬቱን ማስቀጠል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በመሆኑም በተጠናከረ የግለት መንፈስ ለህዝብ ተጠቃሚነት፣ ለምድራችን ደህንነት፣ ለሰላም እና ለብልፅግና መትጋት ይገባል ነው ያሉት።

የተባበሩት መንግሥታት፥ ሀገራት የምግብ ሥርዓትን ለማሻሻል ለሚያደርጉት ጥረት ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025