
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 22/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የምግብ ስርዓት ሽግግርንና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ቁርጠኛ ሆና እንደምትቀጥል ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ ገለጹ።
ላለፉት ሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው ሁለተኛው የምግብ ስርዓት ጉባኤ የማጠናቀቂያ መርሀ ግብር በመካሄድ ላይ ነው።
በመድረኩ የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ታዬ አጽቀስላሴ፣ የጣሊያን መንግስት የምግብ ዋስትና ልዩ መልዕክተኛ ስቴፋኖ ጋቲ እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ጸሀፊ አሚና መሀመድ እና ሌሎች የዓለም ዐቀፍ ተቋማት መሪዎች ተገኝተዋል።
የኢፌድሪ ፕሬዝደንት ታዬ አጽቀስላሴ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ጉባኤው የተካሄደው አለም በፈታኝ ሁኔታ ባለችበት ወቅት ነው።
ሀገራት ዘላቂ የሆነ የምግብ ስርዓት ለመገንባት ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው ገልጸው፤ የምግብ ስርዓት አጀንዳ የሁላችንም ጉዳይ መሆን አለበት ብለዋል።
የምግብ ስርዓትን ለማረጋገጥ ለእውነተኛ የተግባር ስራ በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ሀገራት ሀብታቸውን አንድ ላይ በማሰባሰብ ስትራቴጂዎችን መትከል እንዳለባቸውም አመላክተዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በገንዘብና መድረኮችን በመፍጠር እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎችን ለመፍታት እየደረጋቸው ያሉ ጥረቶች የሚመሰገኑ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የምግብ ስርዓትን ለማረጋገጥ ሀገራት ተግባራዊ ምላሽ በመስጠት በቁርጠኝነት መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
እንቅፋቶችን በዘላቂነት ለመፍታት ምክንያት ተኮር ጥረቶች እንዲሁም ውጤታማ ህዝባዊ ንቅናቄን ማድረግ እንደሚገባ ነው ያመላከቱት።
ኢትዮጵያ ይህን አጀንዳ ለመደገፍ ከመቼውም ጊዜ በላይ ቁርጠኛ ሆና እንደምትቀጥልም ገልጸዋል።
ጅግጅጋ፣መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፡- መንግሥት የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ተመለከተ። የኢትዮጵያ ከተሞች የ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር አህጉራዊ የልማት አጀንዳ ...
Mar 26, 2026
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025