አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 19/2017(ኢዜአ)፦ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ከ900 በላይ የመንግስት አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ ማድረግ መቻሉን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ መሪ ስራ አስፈፃሚ ስዩም መንገሻ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን እውን ለማድረግ በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡
ስትራቴጂው ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በተለያዩ ዘርፎች በርካታ ለውጦች መመዝገባቸውን መሪ ስራ አስፈጻሚው ጠቅሰዋል፡፡
የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት በመዘርጋት፣ የዲጂታል አገልግሎት በማስፋት እንዲሁም ብሔራዊ መታወቂያ ተደራሽ በማድረግ በኩል አመርቂ ሥራዎች መሰራታቸውን ለአብነት አንስተዋል።
በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የዳታ ማዕከላት መገንባታቸውን እንዲሁም የኢንተርኔትና ኤሌክትሪክ አቅርቦት እየተስፋፋ መምጣቱን አብራርተዋል።
በተጨማሪም የሞባይልና የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን መጨመሩንና የዲጂታል የክፍያ ሥርዓት እመርታ እያስመዘገበ መሆኑንም ገልጸዋል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ የ2017 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸምን በገለጹበት ወቅት 16 ከተሞችን በ5 ጂ እና 512 ከተሞችን በ4ጂ ኔትወርክ ተደራሽ ማድረግ መቻሉን መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
በርካታ የሞባይል ጣቢያዎች መገንባታቸውን በማንሳት፥ በአሁኑ ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ10ሺህ በላይ የሞባይል ጣቢያዎች አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ገልጸው፤ የአገልግሎት ተጠቃሚዎቹን ቁጥር 83 ነጥብ 2 ሚሊዮን ማድረስ መቻሉን መግለጻቸውም እንዲሁ።
እስካሁን በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ከ900 በላይ የመንግስት አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ ማድረግ መቻሉን በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ መሪ ስራ አስፈፃሚ ስዩም መንገሻ ገልጸዋል፡፡
የመንግስት አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ ማድረግ የሚሰጡ አገልግሎቶችን እንደሚያሳልጥ አንስተው የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለተጠቃሚዎች ተደራሽ እያደረገ ያለውን ውጤታማ አገልግሎት ለአብነት አንስተዋል፡፡
የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መሰረት መስቀሌ በበኩላቸው፤ የመንግሥት ግዥና አስተዳደር ሥርዓትን ዲጂታላይዝ የማድረግ ተግባር ማከናወኑን ገልፀዋል።
በዚህ አገልግሎት አሰጣጡን ፈጣንና ቀልጣፋ በማድረግ በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ህግና ፖሊሲ ክፍል ባለሙያ ገብርኤላ አብርሃም፤ ለዲጂታል ኢትዮጵያ ግንባታ አስቻይ ሁኔታ ከሚፈጥሩ ጉዳዮች መካከል አንዱ የብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎት መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ የአሰራር ስርዓት ተግባራዊ መሆን ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ በህገ ወጥ መልኩ ሲዘጋጁ የነበሩና ወረቀትን መሰረት ያደረጉ አሰራሮችን ማስቀረት መቻሉን አብራርተዋል።
ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ከ20 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለብሔራዊ መታወቂያ መመዝገባቸው ታውቋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025