የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ከ43 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ

Jul 25, 2025

IDOPRESS

ወልቂጤ፤ ሐምሌ 17/2017(ኢዜአ)፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ማስፈጸሚያ የሚውል ከ43 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አጽድቋል።

‎የክልሉ ምክር ቤት በጀቱን ያጸደቀው በወልቂጤ ከተማ እያካሄደ በሚገኘው 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 4ኛው መደበኛ ጉባኤ ነው።

‎በክልሉ ምክር ቤት የፋይናንስና በጀት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ታመነ ገብሬ የተያዘውን በጀት ለወሳኝ ተቋማት እና እንደሀገር በኢኒሼቲቭ ለሚሰሩ ሥራዎች በአግባቡ እንዲውል ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።


‎እንደ አቶ ታመነ ገለጻ በጀቱ በዋናነት ለጤና፣ ለትምህርት፣ ለድህነት ቅነሳ ሥራዎች፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለሌሎች አገልግሎቶች እንደሚውልም ተናግረዋል።

‎የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ዘይቱና ኢብራሂም በሰጡት ማብራሪያ የበጀቱ ምንጭ የክልሉ የውስጥ ገቢ፣ ከፌደራል መንግስት የሚሰጥ ድጎማ እና ሌሎች የገቢ ምንጮች መሆናቸውን ገልጸዋል።


‎የዘንድሮ በጀት ከአምናው ጋር ሲነፃፀር የ15 በመቶ እድገት እንዳለው ጠቅሰው፣ ከአጠቃላይ በጀቱ 23 ቢሊዮን 724 ሚሊዮን 463 ብር በክልሉ የውስጥ ገቢ የሚሸፈን ይሆናል ብለዋል።

በራስ አቅም የሚሰበሰብ ገቢ እያደገ በመሆኑ ሁሉም መዋቅሮች የገቢ አሰባሰብ አቅማቸውን ለማሳደግ፣ በጀታቸውን በአግባቡ ለማስተዳደርና ግልጽነት መፍጠር ላይ ትኩረት እንዲሰጡ ኃላፊዋ አሳስበዋል።


የምክር ቤቱ አባላት በቀረበው የበጀት ረቂቅ ላይ ሀሳብና አስተያየት ሰጥተው ከተወያዩ በኋላ በጀቱን አጽድቀዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025