ወልቂጤ፤ ሐምሌ 16/2017(ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጀትን በአግባቡ በመጠቀምና የገቢ አቅምን በማሳደግ የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መመለስ ያስቻሉ ተግባራት መከናወናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) ገለጹ።
የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በወልቂጤ ከተማ እያካሄደ ነው።
ርዕሰ መስተዳድሩ የ2017 በጀት ዓመትን አፈጻፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በፖለቲካ ሥራዎች የህዝብን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ተግባራት ተከናውነዋል።
በጀትን በአግባቡ በመጠቀምና የገቢ አቅምን በማሳደግ የህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ተደራሽ ማድረግ ያስቻሉ ተግባራት መከናወናቸውንም ተናግረዋል።
የሰላም ግንባታ፣ የገቢ አቅም ማሳደግ፣ የግብርና ምርታማነት መጨመርና የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማስፋት የተደረጉ ጥረቶች ውጤታማ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
በማህበራዊ ዘርፍም የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነትን ለማስፋት የተደረጉ ጥረቶች ውጤት እንደተገኘባቸው ጠቁመው፣ አጠናክሮ ለማስቀጠል ይሰራል ብለዋል።
በመኸር እርሻ 559ሺህ 592 ሄክታር ማሳ በማልማት ከ51 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰብ መቻሉን በሪፖርቱ አመልክተዋል።
የአፈር ማዳበሪያና ምርጥ ዘር በሁሉም አካባቢዎች በሚፈለገው ልክ በወቅቱ ተደራሽ መደረጉንም ገልጸዋል።
ከተሞችን ለኑሮ ምቹና ተወዳዳሪ ለማድረግ በተጀመረው ስራ የክልል ክላስተር መቀመጫ በሆኑ ሰባት ከተሞች ከ73 ኪሎ ሜትር በላይ የኮሪደር ልማት እየተከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል።
ገበያን ለማረጋጋት ከቅዳሜና እሁድ የገበያ ማዕከላትን በማቋቋም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸው፣ የዜጎችን የሥራ ዕድል ፈጠራ ለማስፋት በተደረገ ጥረት በሀገር ውስጥና በውጭ የሥራ ስምሪት 371ሺህ 355 ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለጹት በንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና በመንገድ መሰረተ ልማት ተደራሽነት ላይም ውጤታማ ሥራዎች ተከናውነዋል።
በማህበራዊ ዘርፍም በትምህርትና በጤና መስክ ህብረተሰቡን በማሳተፍ በተሰሩ ሥራዎች ውጤት መገኘቱን ገልጸዋል።
የክልሉ አፈ ጉባኤ ፋጤ ሰርሞሎ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ምክር ቤቱ ባከናወናቸው የክትትል፣ የቁጥጥርና የድጋፍ ሥራዎች በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ለውጥ ማምጣት መቻሉን ጠቅሰዋል።
ክልሉ ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆንም ዘግይተው የነበሩ የልማት ፕሮጀክቶችና ሌሎች የህዝብ ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ እንዲያገኙ የተጀመሩ ሥራዎች እንዲጠናከሩ ምክር ቤቱ የክትትልና ቁጥጥር ስራውን ያጠናክራል ብለዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025