ወልዲያ፤ ሐምሌ 16/2017(ኢዜአ)፡-በፍራፍሬ ልማት መሠማራታቸው ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እያሳደገው መምጣቱን የሰሜን ወሎ ዞን አርሶ አደሮች ገለጹ።
የዞኑ ግብርና መምሪያ በበኩሉ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ317 ሺህ ኩንታል በላይ የፍራፍሬ ምርት ለገበያ በማቅረብ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ማድረግ እንደታቸለ አስታውቋል።
በሰሜን ወሎ ዞን ሃብሩ ወረዳ ቡሆሮ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ተገኘ ወርቁ ለኢዜአ እንደገለጹት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከማንጎና ፓፓያ ምርት ሽያጭ ከ87 ሺህ ብር በላይ አግኝተዋል።
በአሁኑ ወቅትም ተጨማሪ የማንጎና ፓፓያ ምርቶችን ለገበያ ማቅረባቸውን ገልጸው፣ በቀጣይም ልማቱን በማስፋፋተ በሚያገኙት ገቢ ወደንግድ ስራ ለመሰማራት ማቀደቻውን ተናግረዋል።
በዞኑ ጉባላፍቶ ወረዳ የአላውሃ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ጎበዜ በላይ በበኩላቸው የማንጎ፣ ፓፓያና ሙዝ ምርት ለገበያ በማቅረብ በበጀት ዓመቱ ከ45 ሺህ ብር በላይ ገቢ መግኘታቸውን ተናግረዋል።
ከፍራፍሬ ልማቱ በሚያገኙት ገቢ ቤተሰባቸውን ከማስተዳደር ባለፈ የኢኮኖሚ አቅማቸው እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል።
በሰሜን ወሎ ዞን በመስኖና በመደበኛ እርሻ በ1ሺህ 655 ሄክታር መሬት ላይ ፍራፍሬ መልማቱን የገለጹት ደግሞ በሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ የአትክልትና ፍራፍሬ ቡድን መሪ አቶ አለባቸው መራዊ ናቸው።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በመስኖ ከለማው ፍራፍሬ 317 ሺህ 220 ኩንታል ምርት ለገበያ በማቅረብ አርሶ አደሩን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል።
በልማቱም 82 ሺህ 750 አርሶ አደሮች በመሳተፍ ማንጎ፣ አቡካዶ፣ ፓፓያ፣ ሙዝ፣ አፕል፣ ብርቱካንና ሌሎች ፍራፍሬዎችን በመስኖ ማልማታቸውን ተናግረዋል።
አርሶ አደሮቹ ምርታማነታቸውን ለማሳደግ የግብርና ቴክኖሎጂ ከመጠቀም በተጨማሪ የተሻሻሉ የፍራፍሬ ዝርያዎችን እያለሙ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
ከመምሪያው የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው በ2016 በጀት ዓመት በዞኑ ከ310 ሺህ ኩንታል በላይ የፍራፍሬ ምርት ለገበያ በማቅረብ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተችሏል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025