አምቦ፤ ሐምሌ 14/ 2017 (ኢዜአ)፦ በምዕራብ ሸዋ ዞን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ18 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ 1 ሺህ 500 የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ።
በዞኑ ኤጄሬ ወረዳ የተገነቡ የዲጂታል ፓርክ፣ የማህበረሰብ መድኃኒት ቤት እና የወረዳው የኦሮሚያ ልማት ማህበር ጽህፈት ቤት ህንጻ እና ሌሎች የመሰረተ ልማት ተቋማት ተመርቀዋል።
በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አበበ ጨመዳ እንደገለጹት በዞኑ በህዝብ እና በመንግስት ተሳትፎ የተገነቡ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች በሁሉት ዙር እየተመረቁ ነው።
በዚህም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ18 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ግንባታቸው የተከናወኑ 1 ሺህ 500 የተለያዩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት በቅተዋል።
ለአገልግሎት ከበቁት ፕሮጀክቶች መካከል የትምህርት፣ የጤናና የንጹህ መጠጥ ውሃ ተቋማት እንዲሁም የመንገድ ግንባታ እና ሌሎችም ይገኙበታል ብለዋል።
ፕሮጀክቶቹም የህዝቡን የቆየ የልማት ጥያቄዎች ለመፍታት የተገነቡ መሆኑን ገልጸው ህብረተሰቡም ፕሮጀክቶቹን መጠበቅና መንከባከብ እንዳለበትም አሳስበዋል።
የኤጄሬ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አዱኛ ብሩ በበኩላቸው በወረዳው ለአገልግሎት ከበቁ የልማት ፕሮጀክቶች መካከል የወተት ላሞች እርባታና ከብት ማደለቢያ ማዕከላት፣ የመንገድ መብራት፤ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ዘመናዊ ቤተ-መጻህፍት፣ የጤና ጣቢያና የመንገድ ግንባታን ያካተተ መሆኑን ገልጸዋል።
በወረዳው በአጠቃላይ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የመሰረተ ልማት ተቋማት ለአገልግሎት በቅተዋል ብለዋል።
ኢዜአ ያነጋገራቸው በዞኑ የኤጄሬ ወረዳ ነዋሪዎችም በአካባቢያቸው ለአገልግሎት የበቁ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች የረጅም ጊዜ ጥያቄያቸውን የሚመልሱ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ወይዘሮ ባዳቱ ጫካ እንዳሉት አሁን ላይ በቀበሌያቸው የተገነባው ጤና ጣቢያ አገልግሎት መስጠት በመጀመሩ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ረጅም ርቀት ከመጓዝ እንደታደጋቸው ተናግረዋል።
ሌላኛው የወረዳው ነዋሪ አቶ ጥላሁን ቲክሴ በበኩላቸው፤ በተለይ በክረምት ወቅት ከባድ የመንገድ ችግር እንደነበረ ጠቅሰው አሁን ላይ የተገነባው መንገድ በአካባቢው የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዲጠናከር የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025