የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ልማት እንዲጠናከር ግብራችንን በወቅቱና በታማኝነት እየከፈልን ነው - ግብር ከፋዮች

Jul 18, 2025

IDOPRESS

ወልቂጤ፤ ሐምሌ 10/2017(ኢዜአ)፦ ግብርን በወቅቱና በታማኝነት በመክፈል የልማት ሥራዎች እንዲጠናከሩ የድርሻቸውን እየተወጡ መሆኑን የጉራጌ ዞን ግብር ከፋዮች ተናገሩ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ በበኩሉ ገቢን በአግባቡ በመሰብሰብ ወጪን በራስ አቅም ለመሸፈን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።


በክልሉ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ግብር ከፋይ አቶ ከበደ ቢረዳ ግብርን በታማኝነት በመክፈላቸው የልማት ተጠቃሚነታቸው እያደገ መምጣቱን ጠቁመዋል።

ዘንድሮም ግብርን በታማኝነት የመክፈል ተግባራቸውን አጠናክረው ከመቀጠል ባለፈ ለሚፈጽሙት ግብይትና አገልግሎት ደረሰኝ የመጠየቅ ልምድ እያዳበሩ መምጣታቸውን ገልጸዋል።


የገቢ ግብርን በወቅቱና በታማኝነት በመክፈል ልማትን መጠየቅ አግባብ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በቸሃ ወረዳ የጃካ ከተማ ነዋሪዋ ግብር ከፋይ ወይዘሮ ገሽግሽ ደምስ ናቸው።

ግብር ልማትን ለማፋጠን ያለውን ፋይዳ በመረዳታቸው በየዓመቱ ግብራቸውን በታማኝነትና በወቅቱ በመክፈል ሃላፊነታቸውን እየተወጡ መሆኑንም ተናግረዋል።


በአካባቢያቸው የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ግብርን በወቅቱ በመክፈል የድርሻቸውን እየተወጡ መሆኑን የገለጹት ደግሞ አቶ ሰለሞን ይርጋ ናቸው።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአካባቢያቸው የልማት እንቅስቃሴ እየተፋጠነ መሆኑን ገልጸው፣ ይህን አጠናክሮ ለማስቀጠል ሁሉም የሚጠበቅበትን ግብር በወቅቱ መክፈል እንዳለበት ገልጸዋል።


በጉራጌ ዞን ገቢዎች ጽህፈት ቤት የደንበኞች አገልግሎት፣ የታክስ አወሳሰንና አሰባሰብ ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ ስዋሊህ ጀማል እንዳሉት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ3 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል።

ይህም ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል።

በተያዘው በ2018 በጀት ዓመት በአጠቃላይ ከ4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱንም ጠቁመዋል።


የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ምክትል እና የታክስ ህጎች ማስከበር ዘርፍ ሃላፊ ሰለሞን ውድነህ እንደገለጹት የክልሉንገቢ የመሰብሰብ አቅም በማሳዳግ የክልሉን ልማት ለማጠናከር ትኩረት ተሰጥቷል።

በዚህም በ2017 በጀት ዓመት ከቀጥታ ታክስ፣ ቀጥታ ካልሆኑ ታክሶችና ከሌሎች የገቢ ርዕሶች ከ16 ነጥብ 227 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል።

ይህም በ2016 በበጀት ዓመት ከተሰበሰበው ገቢ ጋር ሲነጻጸር ከ5 ቢሊዮን 404 ሚሊዮን ብር በላይ ብልጫ እንዳለው አመልክተዋል።

የግብር መክፈያ አማራጮችን ምቹ ከማድረግ ባለፈ ማዕከላትን በየአካባቢው ተደራሽ በማድረግ ግብር ከፋዩ ማህበረሰብ በአቅራቢያው አገልግሎት ማግኘት እንዲችል መደረጉ ለተገኘው ውጤት አስተዋጽኦ ማድርጉን ገልጸዋል።

በተያዘው የሐምሌ ወርም የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች በተቀናጀ መንገድ የሚጠበቅባቸውን ግብር በወቅቱና በታማኝነት እንዲከፍሉ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025