የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ኢጋድ ለአህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ትግበራ በቁርጠኝነት መስራቱን ይቀጥላል

Jul 14, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 5/2017(ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) ለአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ተፈጻሚነት በቁርጠኝነት መስራቱን እንደሚቀጥል የተቋሙ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር) ገለጹ።

47ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት እና 7ኛው የህብረቱ ቀጣናዊማህበረሰቦች የመንፈቅ ዓመት የጋራ የትብብር ስብሰባ በኢኳቶሪያል ጊኒ ማላቦ እየተካሄደ ይገኛል።


በተጓዳኝም ሶስተኛው በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ትግበራ ላይ ያተኮረ የቀጣናዊ ማህበረሰቦች ኃላፊዎች የጋራ ስብሰባ ተካሂዷል።

ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች የተቀናጀ የመሰረተ ልማት ትስስር፣ የንግድ ልውውጥና የፖሊሲ ተጣጣሚነትን በመፍጠር የአፍሪካን የኢኮኖሚ ትስስር እውን በማድረግ ያላቸው ቁልፍ ሚና በስብሰባው ተነስቷል።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር) በስብሰባውስለ ኢጋድ ቀጣናዊ የመሰረተ ልማት ማስተር ፕላን ያነሱ ሲሆን ማዕቀፉ ከአፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጣና እና አጀንዳ 2063 ጋር የሚመጋገብ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢጋድ ለአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራ በቁርጠኝነት መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውን ኢዜአ ከተቋሙ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025