ወልቂጤ፤ ሐምሌ 2/201`7 (ኢዜአ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የገጠር ኮሪደር ልማት የማህበረሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በሚያሳድግ መልኩ የማስፋፋት ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለጹ።
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በክልሉ በ10 የገጠር ወረዳ አስተዳደሮች ተግባራዊ የሚደረግ የገጠር ኮሪደር ልማት መርሃ ግብርን በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ አበኬ ቀበሌ አስጀምረዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ የገጠር ኮሪደር የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነትን በሚያሻሻል መልኩ እየተገበረ ነው ብለዋል።
በክልሉ እየተተገበረ ያለው የገጠር ኮሪደር ልማት የአርሶ አደሩን የኑሮ ዘይቤ ከማሻሽል ባለፈ ውብና ጽዱ አካባቢን የመፍጠር ዓላማ ያለው እንደሆነ ገልጸዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ የገጠር ኮሪደር ማሳያ የሆነው የጉራጌው ጀፎረ የቀደምት አባቶች የአርቆ አሳቢነት ውጤት መሆኑን ጠቅሰው የገጠር ኮሪደር በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች እንዲተገበር በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
በአስተዳደሮቹ የሚከናወኑ የገጠር ኮሪደር ልማት በራስ አቅም የሚፈፀም መሆኑን ያነሱት ርዕሰ መስተዳድሩ አተገባበሩ ላይ ህዝቡ፣ ባለሀብቱና ተቋማት በቅንጅት መሳተፍ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡
የገጠር ኮሪደር ልማት የሰዎችና የእንሳት ቤት እንዲሁም መፀዳጃና የባዮጋዝ ማብሊያ ግንባታ ያካተተ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር በበኩላቸው በክልሉ የተጀመረው የገጠር ኮሪደር ልማት የአርሶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻልና ሀብት ለመፍጠር ያለመ ነው ብለዋል፡፡
ግብርናን ለማዘመን፣ ቀጣይነት ባለው መልኩ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ፣ አርሶ አደሩ ሀብት ፈጥሮ ተረጋግቶ መኖር እንዲችል የሚያግዝ መሆኑንም ገልጸዋል።
የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንዳሉት የጉራጌ ጀፎረ ማራኪ የመንደር ገጽታ ያለው፣ አረንጓዴ ሳር የለበሰ የቀደምት አባቶች አሻራ ነው።
ጀፎረ ሁሉም በባለቤትነት የሚጠብቀው፣ የሚንከባከበው እና የጋራ መጠቀሚያ መሆኑን አስታውሰው በዞኑ ባህሉን የማጠናከር ስራ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
በጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ ነዋሪ አቶ አለሙ በስር፤ የገጠር ኮሪደር የአርሶ አደሩ ኑሮ ለማሻሻል የሚያስችል እና ጀፎረም ይበልጥ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ የሚያስችል ነው ብለዋል።
''የኮሪደር ልማት ስራው የራሳችንን አከባቢ የሚያሳምር በመሆኑ ተቀብለን እያጠናከርነው ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
ጀፎረ ውብና ማራኪ አካባቢ ከመፍጠር ባለፈ ለማህበራዊ ክዋኔዎች ወሳኝ መሆኑን የጠቀሱት ደግሞ ሌላው የወረዳው ነዋሪ አቶ በሽር አግዜ ናቸው።
ስራውን የበለጠ ለማጠናከር በቀበሌያቸውና በመንደራቸው እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025