አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 2/2017(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ የሥራ ፈጠራ ፎረም የአህጉሪቱ ወጣቶችና ሥራ ፈጣሪዎች ያላቸውን ትስስር እንዲያጠናክሩ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለፁ።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀውና በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሲካሔድ የቆየው የአፍሪካ የሥራ ፈጠራ ፎረም የማጠናቀቂያ መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው።
በመርኃ ግብሩ ላይ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራች ነው።
በሀገሪቱ ወጣቶች ሥራ ፈጣሪና የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት መመዝገቡንም ጠቅሰዋል።
በተለይም አማራጭ የሥራ እድሎችን የማስፋት፣ በየዘርፉ የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችን የማስረፅና ወጣቱ በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ያለውን ተሳትፎ ማጉላት ዋነኞቹ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በዚህ ረገድ ላለፉት ሦስት ቀናት ሲካሔድ የቆየው የሥራ ፈጠራ ፎረም የአህጉሪቱ ወጣቶችና ሥራ ፈጣሪዎች ያላቸውን ትስስር እንዲያጠናክሩ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን አስታውቀዋል።
መድረኩ በተለይም የልምድ ልውውጥ በማድረግ ተሞክሯቸውን እንዲጋሩ እና በዘርፉ ለሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች የጋራ መፍትሄ ለማበጀት አስቻይ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ማድረጉን ገልጸዋል።
ፎረሙ የአፍሪካ ሀገራት በቀጣይ በዘርፉ በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ስምምነት ከማድረግ ባለፈ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀመጡበት መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡
አፍሪካ ቀጣይነት ያለው ልማትን እንድታረጋግጥ በኢኮኖሚ፣ በልማትና በመሰረተ ልማት ማስተሳሰር የጋራ ርብርብና ጥረትን የሚጠይቅ ስለመሆኑም አብራርተዋል።
በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በሥራ እድልና በተለያዩ ዘርፎች ከአህጉሪቱ ሀገራት ጋር ያላትን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025