ደሴ፤ ሐምሌ 2/2017(ኢዜአ) ፡-በደቡብ ወሎ ዞን በ2017 የበጀት ዓመት ከ235 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራን በማከናወን ለአገልግሎት ምቹ በመደረጉ የሕብረተሰቡን ችግር ማቃለል መቻሉ ተገለጸ።
በበጀት ዓመቱ ለመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራ ወጪ የተሸፈነው ከመንግስትና ከሕብረተሰቡ በተገኘ ድጋፍ መሆኑን የደቡብ ወሎ ዞን መንገድ መምሪያ አስታውቋል።
የመምሪያው ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ሐሰን፤ በዞኑ የመንገድ ተደራሽነትን በማስፋትና በአገልግሎት ብዛት የተጎዳን በመጠገን ለአገልግሎት ለማብቃት ሲሰራ መቆየቱን ለኢዜአ ተናግረዋል።
በዚህም በበጀት ዓመቱ 173 ኪሎ ሜትር አዲስ የጠጠር መንገድ ግንባታ እና አንድ ሺህ 266 ኪሎ ሜትር የተጎዳ ነባር መንገድን ለአገልግሎት ማብቃት መቻሉን አስታውቀዋል።
መንገዱ ቀበሌን ከቀበሌ፣ ቀበሌን ከወረዳ፣ ወረዳን ከወረዳ እና ከዞን የሚያገናኙ ናቸው ያሉት ኃላፊው ፤ በተጨማሪ ሁለት ተንጠልጣይ እና አንድ ኮንክሪት ድልድዮችም መገንባታቸውን ጠቁመዋል።
ይህም ለሕብረተሰቡ ጥያቄ ምላሽ በመስጠት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎችን ለማነቃቃትም ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።
ሕብረተሰቡ የአከባቢውን ሰላም በመጠበቅ ከመንግስት ጎን ተሰልፎ በጉልበቱ፣ በሀሳቡና በገንዘቡ ላደረገው ተሳትፎም ምስጋና አቅርበዋል።
በቃሉ ወረዳ የ029 ቀበሌ ነዋሪ አቶ ሁሴን ኢብራሂም በሰጡት አስተያየት፤ ከቀበሌያቸው እስከ አርዲቦ ያለው መንገድ በአገልግሎት ብዛት በመበላሸቱ ተቸግረው እንደቆዩ አስታውሰዋል።
ዘንድሮ በተሻለ ሁኔታ ተጠግኖ ለአገልግሎት ምቹ በመደረጉ ችግራቸው መቃለሉን ተናግረዋል።
የወረባቦ ወረዳ ነዋሪ አቶ ሰይድ ፈንታው በበኩላቸው፤ በአካባቢያቸው የተሽከርካሪ መንገድ ባለመኖሩ ምርታቸውን ለገበያ ለማቅረብና ሕመምተኛን ወደ ህክምና ለመውሰድ አዳጋች ሆናባቸው መቆየቱን አመልክተዋል።
ዘንድሮ አዲስ መንገድ ተሰርቶላቸው ተሽከርካሪም እየመጣ እንደልባቸው መንቀሳቀስ በመጀመራቸው መደሰታቸውን ገልጸው፤ ለመንገዱ ግንባታ በጉልበታቸውና በገንዘባቸው የድርሻቸውን መወጣታቸውንም ተናግረዋል።
በዞኑ በበጀት ዓመቱ ለተከናወነው የመንገድ ግንባታና የጥገና ሥራ በመንግስትና ሕብረተሰቡ ከ235 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉን ከመንገድ መምሪያው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025