ወልዲያ፤ ሰኔ 30/2017(ኢዜአ) ፡-የተፈጥሮ ማዳበሪያ አዘጋጅተው መጠቀማቸው የአፈር ለምነትን በማሻሻል ምርታማነትን ከማሳደግ በሻገር ለማዳባሪያ ግዥ ያወጡት የነበረን ገንዘብ ማስቀረቱን በሰሜን ወሎ ዞን አርሶ አደሮች ገለጹ።
የዞኑ ግብርና መምሪያ በበኩሉ ለበልግና ለመኸር እርሻ ልማት ከ4 ነጥብ 9 ሚሊዮን በላይ ሜትር ኪዩብ የተፈጥሮ ማዳበሪያ መዘጋጀቱን አስታውቋል።
በዞኑ ሃብሩ ወረዳ የቁጥር አምስት ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር አያሌው አበራ ለኢዜአ እንደገለጹት ባለፉት ሦስት ዓመታት የተፈጥሮ ማዳበሪያ በማዘጋጀት ሦስት ጥማድ መሬታቸውን ሲያለሙ ቆይተዋል።
የተፈጥሮ ማዳበሪያው ለምርታማነት መጨመር ያለውን ፋይዳ በተግባር በማየታቸውም ዘንድሮም 16 ኩንታል ኮምፖስት በማዘጋጀት ለተያዘው የመኸር እርሻ ጥቅም ላይ እያዋሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዚህም ዘንድሮ ለዘመናዊ ማዳበሪያ ግዥ ያወጡት የነበረን 17ሺህ 700 ብር ለማዳን መቻላቸውን ገልጸዋል።
በጉባላፍቶ ወረዳ የአማዬ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ደሳለ ጉግሳ በበኩላቸው፣ የተፈጥሮ ማዳበሪያ የአፈር ለምነትን ከማሻሻል በተጨማሪ ወጪን ለመቀነስ እያገዛቸው መሆኑን ተናግረዋል።
ዘንድሮ ከ14 ኩንታል በላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ማዘጋጀታቸውን ጠቁመው፣ በአሁኑ ወቅትም በእርሻ መሬታቸው ላይ ማዳበሪያውን በመበተን የማዋሃድ ሥራ እያከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የተፈጥሮ ማዳበሪያ እርጥበትን አቅቦ በመያዝ ምርታማነትን ለማሳደግ ጉልህ ድርሻ እንዳለው ገልጸው፣ በቀጣይም የተፈጥሮ ማዳበሪያ አዘጋጅተው መጠቀማቸውን እንደሚያጠናክሩ ተናግረዋል።
የምግብ ሉአላዊነትን ለማረጋገጥ ለተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ የአፈር ለምነት ማስፋፊያና ማሻሻያ ባለሙያ አቶ ደርቤ አያሌው ናቸው።
ዘንድሮም ከ4 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ሜትር ኪዩብ የተፈጥሮ ማዳበሪያ፣ 17 ሺህ 934 ሜትር ኪዩብ ባዮ ሳለሪ ኮምፖስት እና 136 ሺህ 582 ኩንታል ቨርሚ ኮምፖስት መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
በኮምፖስት ዝግጅቱ 330 ሺህ 638 አርሶ አደሮች መሳተፋቸውን የገለጹት ባለሙያው፣ የተዘጋጀው የተፈጥሮ ማዳበሪያም 140 ሺህ ሄክታር የሚጠጋ መሬት በማልማት ምርታማነትን ለማሳደግ እንደሚያስችልም አስረድተዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025