ሚዛን አማን፣ ሰኔ 28/2017 (ኢዜአ)፦በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከተሞችን ለሥራና ለኑሮ ምቹ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ ዓለሙ ገለጹ።
የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ ዓለሙ እንዳሉት ከተሞችን ለነዋሪው ለሥራና ለኑሮ ምቹ ለማድረግ እየተሰራ ነው።
በዚህም በክልሉ አራት ብዝኃ ዋና ከተሞች ላይ በ450 ሚሊዮን ብር በጀት የኮሪደር ልማት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በእስካሁኑም 4 ነጥብ 9 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ስራ ለማከናወን መቻሉን ተናግረዋል።
በኮሪደር ልማት ሥራው የኅብረተሰቡ ሚና የጎላ መሆኑን አንስተው ፕሮጀክቶች በፍጥነት እንዲጠናቀቁና ልማቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠንካራ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ዋና ማዘጋጃ ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ወንድሙ አለማየሁ በከተማዋ በመጀመሪያ ዙር እየተገነባ ያለው 1 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ሥራ 95 በመቶ መድረሱን ተናግረዋል።
ስራውን በማስቀጠል በ2018 በጀት ዓመት ከ5 ኪሎ ሜትር በላይ የሚሸፍን የኮሪደር ልማት ሥራ ለማከናወን መታቀዱንም ጠቅሰዋል።
ኅብረተሰቡ በከተማዋ እየተከናወኑ ላሉ የልማት ሥራዎች ትብብሩን እያሳየ መሆኑንም አመልክተዋል።
ከከተማዋ ነዋሪዎች መካከል አቶ ጌታሁን ሻዎ እና ወጣት አበበ ሻምፕቴት በመጀመሪያ ዙር የኮሪደር ሥራ በለሙ አረንጓዴ ሥፍራዎች ለመዝናኛ እና አዕምሮን ለማሳረፍ እያገለገሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ልማቱን ይበልጥ በማስፋፋት ለከተማዋ ዕድገት የሚያበርክተውን አስተዋጽኦ ማጉላት እንደሚገባ አክለዋል።
የኮሪደር ልማት የትራፊክ መጨናነቅን ማስቀረት፣ የከተማ ዕድገት ማረጋገጥና ጽዱና ምቹ መኖሪያ አካባቢን መፍጠር ያስችላል ብለዋል።
በቀጣይም ልማቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025