አርባ ምንጭ፤ ሰኔ 26/2017(ኢዜአ) ፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኢኮኖሚ ሽግግርን ለማሳለጥ የኢንዱስትሪውን ዘርፍ በጥናትና ምርምር ለማገዝ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ።
ክልል አቀፍ የኢንዱስትሪ እምቅ አቅም ልየታ ምርምር ውጤት ላይ ያተኮረ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ዛሬ በአርባ ምንጭ ከተማ ተካሂዷል።
በመድረኩ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር እንዲሳለጥ የኢንዱስትሪ ዘርፍ እምቅ ፀጋዎችን በጥናትና ምርምር ለማገዝ እየተሰራ ነው።
በክልሉ ልማትን ለማረጋገጥ ዘርፉ ያለውን አቅም ለይቶ ለማጠናከር በቅንጅት እንደሚሰራ ጠቅሰው፣ ለዚህም የዘርፉን እምቅ አቅም መለየት ፋይዳው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚስተዋሉ የምርታማነት፣ የአቅም እና የድጋፍ አሰጣጥ ማነቆዎችን በመፍታት ሰፊ መደላድል በመፍጠሩ ውጤት እየተመዘገበ ነው ያሉት አበባየሁ (ዶ/ር)፣ በቀጣይም ይህን ማስፋት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
አቅምን ባለማወቅ የኢንዱስትሪ ልማትን በሚፈለገው ልክ ማረጋገጥ እንዳልተቻለ ገልጸው፣ የዘርፉን አቅም በመለየትና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ለማሳካት በቁርጠኝነት ይሰራል ብለዋል።
የክልሉ ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ ቦጋለ ቦሼ (ዶ/ር) በበኩላቸው እንዳሉት በክልሉ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግርን ለማረጋገጥ የኢንዱስትሪ እምቅ ፀጋዎችን ጥቅም ላይ ለማዋል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው።
ባለፉት ሁለት ዓመታት በዘርፉ በተከናወኑ ተግባራት በክልሉ የኢንዱስትሪ ዘርፍ 12 ነጥብ 6 በመቶ ዕድገት መመዝገቡንም ተናግረዋል።
በጥናትና ምርምር ታግዞ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ተገቢውን ድጋፍ ለማድረግ ከአርባ ምንጭ፣ ከወላይታ ሶዶ፣ ከዲላ እና ጂንካ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ዘርፉን በማዘመንና ምርታማነት በማሳደግ ከተኪና ወጪ ምርቶች የሚገኘውን የውጭ ምንዛሬ በማሳደግ የክልሉንና የሀገርን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ቦጋለ (ዶ/ር) አስታውቀዋል።
የጥናት ውጤቱን ያቀረቡት የክልሉ ፖሊሲ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ በረከት ረጋሳ (ዶ/ር) በተደረገው ጥናት መሠረት በክልሉ የኢንዱስትሪውን እንቅስቃሴ የሚያሳልጡ የተፈጥሮ ጸጋዎችና አምራች ሃይል መኖሩን ገልጸዋል።
በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በማዕድን፣ በኮንስትራክሽንና በቱሪዝም ዘርፍ የክልሉን ኢኮኖሚያዊ መዋቅራዊ ሽግግር የሚያሳልጡ አቅሞች በጥናቱ መዳሰሳቸውን አስረድተዋል።
በዘርፉ ያለውን እምቅ አቅም ለማወቅ የተደረገው ጥናት የክልሉን ኢኮኖሚ ለማፋጠን፣ የህዝብን የነፍስ ወከፍ ገቢ ለማሳደግ እና የሥራ ዕድል ለመፍጠር ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረውም አስገንዝበዋል።
ኢንስቲትዩቱ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር የክልሉን የኢንዱስትሪ ዘርፍ ፀጋዎች፣ ተግዳሮቶችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች በማዘጋጀት በቀጣይ በሀገሪቱ እድገት ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ ለማድረግ ይሰራል ብለዋል።
ለአንድ ቀን በተካሄደው መድረክ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዩኒቨርሲቲ ተወካዮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን የጥናቱን ውጤት ወደ ተግባር መቀየር በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ውይይት ተደርጓል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025