የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በሁሉም የአገሪቷ አካባቢዎች የተገነቡ ከ20ሺህ በላይ ፕሮጀክቶች ይመረቃሉ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Jul 4, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 26/2017(ኢዜአ)፦ በሁሉም የአገሪቷ አካባቢዎች የተገነቡና የህብረተሰቡን የኑሮ ሁኔታ የሚያሻሽሉ ከ20ሺህ በላይ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 42ኛ መደበኛ ስብስባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እያካሄደ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት የመንግስት የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ናቸው።

የምክር ቤቱ አባላት በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ፣ ዲፕሎማሲ እና በሌሎች ጉዳዮች ጥያቄና አስተያየታቸውን አቅርበዋል።

የኮሪደር ልማትን በሚመለከት በሁሉም የአገሪቷ ከተሞች የሚካሄዱ ልማቶች አሳታፊነት ላይ ከምክር ቤቱ ለቀረበላቸው ጥያቄ መንግስት ከኮሪደር በተጨማሪ በርካታ የልማት ስራዎች ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

ከዚህ መካከል መንግስት የህብረተሰቡን የኑሮ ሁኔታ የሚያሻሻሉና በማህበረሰቡ ሲጠየቁ የቆዩ መሰረተ ልማቶችን በማሟላት ረገድ በቁርጠኝነት እየሰራ ስለመሆኑም ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት እስከ ነሃሴ መጨረሻ ድረስ የሚመረቁ ከ20 ሺህ በላይ ፕሮጀክቶች መገንባታቸውን ጠቁመዋል።

ፕሮጀክቶቹ የህብረተሰቡን የኑሮ ሁኔታ የሚያሻሽሉ የጤና ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶችና መሰል የመሰረተ ልማት ስራዎች መሆናቸውን አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025