የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በክልሉ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የዘርፉን ዕድገት የሚመጥን ብቃት እንዲኖራቸው ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው

Jun 27, 2025

IDOPRESS

ሆሳዕና፤ ሰኔ 19/2017 (ኢዜአ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የዘርፉን ዕድገት የሚመጥን ብቃት እንዲኖራቸው ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው ከክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ጋር በመቀናጀት የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ብቃት ማረጋገጫ አሰጣጥ ላይ ያዘጋጀው የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል፡፡


የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ኑሪ ከድር በዚህ ወቅት እንዳሉት ክልሉን ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ በተሰሩ ሥራዎች አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል።

ውጤቶቹን ለማስቀጠል በክልሉ የሚገኙ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወቅቱን የዋጀና የዘርፉን ዕድገት የሚመጥን ብቃት ሊኖራቸው እንደሚገባ ገልጸው፣ ተቋማቱን የማብቃትና የማጠናከር ሥራ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በክልሉ በሆቴል ኢንቨስትመንትና በሌሎች የዘርፉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የሚታየውን ውስንነት ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን ተናግረው፣ የዛሬው የምክክር መድረክም የእዚሁ አካል መሆኑን አመልክተዋል።

እንደ አቶ ኑሪ ገለጻ፣ ተቋማቱ ለቱሪስቶች የተሟላ አገልግሎት ከማቅረብ አኳያ ውስንነት እንዳለባቸው በተደረገ ድጋፍና ክትትል ተለይቷል።

ውስንነቶችን ለመፍታት እንደሚሰራ ገልጸው በተለይ ከፍተኛ ድርሻ ያለው የሆቴል አገልግሎት ዘርፍ ተወዳዳሪ እንዲሆን የአገልግሎት አሰጣጥ ብቃት ማረጋገጫ እንዲያሟሉ ለማድረግ ትኩረት መሰጠቱንም አስታውቀዋል።

የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ቀመሪያ ረሻድ በበኩላቸው፣ ቢሮው በንግዱ ዘርፍ የማህበረሰቡን ደህንነት ለማስጠበቅ የወጣውን አዋጅ ለማስተግበር እየሰራ ይገኛል ብለዋል።


በክልሉ ከሆቴል አገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ በርካታ ችግሮች እንዳሉ ጠቁመው፣ ችግሮቹን ለመፍታት የድጋፍና ክትትል ሥራ በመከናወን ላይ መሆኑንም አመልክተዋል።

ተቋማቱ የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉና ለዘርፉ መዘመንና ዕድገት የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ህጋዊ መሰረት ኖሯቸው እንዲንቀሳቀሱ የማድረግ ስራም ይሰራል ብለዋል፡፡

በጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ የቱሪዝም አገልግሎት ብቃት ማረጋገጫ የሥራ ሂደት ቡድን መሪ ወይዘሮ ወይንሸት ሰተቱ በበኩላቸው እንዳሉት፣ በዞኑ በቱሪስት መዳረሻዎች የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ ነው።


ይህም የቱሪስቶችን የቆይታ ጊዜ በማራዘም ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ ይረዳል ያሉት ቡድን መሪዋ፣ ለስኬቱም በሆቴሎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን የማሻሻልና የማብቃት ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

በአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን የማረምና የማስተካከል ሥራዎች እንደሚከናውኑም ገልፀዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የዞንና የልዩ ወረዳ የባህል ቱሪዝም እና የንግድና ገበያ ልማት ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025