የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የጋምቤላ ከተማ የኮሪደር ልማት በጥራትና በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ትኩረት ተሰጥቷል - ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ

Jun 24, 2025

IDOPRESS

በጋምቤላ፤ ሰኔ 16/2017(ኢዜአ)፦ የጋምቤላ ከተማ የኮሪደር ልማት በጥራትና በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ትኩረት መሰጠቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ ገለፁ።

በጋምቤላ ከተማ የኮሪደር ልማት ግንባታ ላይ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በጋምቤላ ከተማ ተወያይተዋል።።

ርዕሰ መስተዳድሯ በመድረኩ እንዳሉት በክልሉ የኮሪደር ልማት ዘግይቶ ቢጀመርም በጥሩ አፈፃፀም ላይ ይገኛል።

በጋምቤላ ከተማ ለኮሪደር ልማት ስምንት የተመረጡ ቦታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው በመጀመሪያው ምዕራፍ በአራት ዋና ዋና መንገዶች ላይ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።


በጋምቤላ ከተማ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ጥራትና ፍጥነቱን ጠብቆ እንዲጠናቀቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

የክልሉ ህዝብም ለኮሪደር ልማቱ ባለው አወንታዊ አመለካከት ለልማቱ ትብብር እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በክልሉ ርዕሰ ከተማ ጋምቤላን ጨምሮ በገጠር ከተሞች ለሚከናወነው የኮሪደር ልማቶች ስኬታማነት ኮሚቴ ተዋቅሮ ሀብት የማሰባሰብ ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል።


በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ካሊድ አብዱረህማን በበኩላቸው በክልሉ የኮሪደር ልማት ዘግይቶ ቢጀመርም አፈፃፀሙ አበረታች መሆኑን አንስተዋል።

የውይይት መድረኩ አላማም በክልሉ እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት አፈፃፀም በመገምገም ውስንነቶቹ ላይ ድጋፍ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።


በጋምቤላ ከተማ እየተተገበረ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ሀገር አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ መተግበሩን በመከታተልና በመቆጣጠር በኩል ትኩረት ይፈልጋል ብለዋል።

በተለይም የኮሪደር ልማቱ የመብራት፣ የስልክ፣ የውሃና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን አቀናጅቶ ለመተግበር የተጀመረው ስራ ሊጠናከር የሚገባው መሆኑን አንስተዋል።

ከውይይት መድረኩ በኃላ በጋምቤላ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘውን የመጀመሪያ ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025