የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

ለህክምናው ዘርፍ 130 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ሀብት እየተበጀተ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Jun 23, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 15/2017(ኢዜአ)፦ መንግስት ለህክምናው ዘርፍ 130 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ሀብት እየበጀተ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከመላው ኢትዮጵያ ከተውጣጡ የጤና ባለሞያዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስት የጤናውን ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

በዚህም ባለፉት አመታት ወደ ለጤና ዘርፉ እየመደበ ያለውን በጀት እያሳደገ ይገኛል ብለዋል፡፡


ከጥቂት አመታት በፊት በቀጥታ ለጤናው ዘርፍ ይመደብ የነበረው ሀብት 70 ቢሊየን ብር ገደማ እንደነበር አስታውሰው፤ በአሁኑ ወቅት መንግስት 130 ቢሊየን የሚጠጋ ሀብት መመደቡን አስታውቀዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ባለፈው ዓመት መንግስት 9 ቢሊዮን ብር ለመድሃኒት ግዥ ድጎማ ማድርጉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

መንግስት ለህክምናው ዘርፍ የሚያወጣው ወጪ ከየትኛውም ጎረቤት ሀገራት እንደሚበልጥም ተናግረዋል።

በጤናው ዘርፍ መንግስት ለግንባታ የሚያወጣውን ወጪ የትኛውም ጎረቤት ሀገር እንደማያወጣ ጨምረው አንስተዋል።

ምንም እንኳን ለጤናው ዘርፍ የሚበጀተው በጀት እያደገ ቢሆንም ካለው ፍላጎት አንጻር ገና መሆኑን ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቷል

ጅግጅጋ፣መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፡- መንግሥት የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ተመለከተ። የኢትዮጵያ ከተሞች የ...

Apr 1, 2026

የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር የልማት አጀንዳ ነው

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር አህጉራዊ የልማት አጀንዳ ...

Mar 26, 2026

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025