የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

አዋጁ ሽብርተኝነትንና ወንጀልን መከላከልና መቆጣጠር የሚያስችል ነው - የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት

Jun 20, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 12/2017(ኢዜአ)፦ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ንብረት ወይም ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የተሻሻለው አዋጅ ሽብርተኝነትንና ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል እንዲሁም ከዓለም አቀፍ ህጎች ጋር የተጣጣመ መሆኑን የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ።

በወንጀል ድርጊት የተገኘን ንብረት ወይም ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የወጣውን አዋጅ ቁጥር 780/2005ን ለማሻሻል የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1387/2017 ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁ ይታወቃል።

በተሻሻለው አዋጅ ዙሪያ ለህብረተሰቡ ተጨማሪ መረጃን ተደራሽ ለማድረግም የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሙሉቀን አማረ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም የተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 1387/2017 ከነባር አዋጁ 780/2005 በ58 አንቀጾች 14ቱ ላይ ማሻሻያ አድርጓል ብለዋል።

አዋጁ ሽብርተኝነትንና ወንጀልን መከላከልና መቆጣጠር የሚያስችል እንዲሁም ከዓለም አቀፍ ህጎች ጋር የተጣጣመ መሆኑን ተናግረዋል።

የማሻሻያ አዋጁ በወንጀል ተግባር የተገኘ ገንዘብን ወይም ንብረትን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀል ድርጊትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚደረገው ዓለም አቀፍ ጥረት ላይ ኢትዮጵያ ድርሻዋን በአግባቡ እንድትወጣ ያስችላል ብለዋል።

አዋጁ አመንጪ የሚባሉ 21 ወንጀሎችን በአባሪነት ያስቀመጠ ብሎም ለትርጉም ተጋላጭ የነበሩ ጉዳዮችን በግልጽ የሚየስቀምጥ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህም ተገቢ ምርመራ ለማካሄድ እንደሚጠቅም ገልጸዋል።

በወንጀል ድርጊት የቅጣት አለመመጣጠን መልክ ማስያዝ የሚያስችል ጭምር መሆኑንም ተናግረዋል።

በሽፋን ስር ለሚደረጉ የምርመራ ሂደቶች ወይንም ልዩ የምርመራ ሂደቶች በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ብቻ የሚከናወን መሆኑን ማስቀመጡን ገልጸዋል።

ይህም ፍርድ ቤቱ በመደበኛ የምርመራ ዘዴ ማስረጃ ማግኘት አዳጋች መሆኑን አምኖ በሰጠው ፈቃድና ትዕዛዝ መሠረት የሚከናወን መሆኑንም ጠቁመዋል።

ይህ የምርመራ ዘዴ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሚደረግ መረጃን ለማግኘት በጥብቅ ዲሲፕሊን እና በፍርድ ቤት ቁጥጥር ስር የሚከናወን መሆኑንም ገልጸዋል።

በአጠቃላይም የተሻሻለው አዋጅ የሀገርን ደህንነትና የህዝብን ጥቅም የሚያስጠብቅ መሆኑን ነው አቶ ሙሉቀን አማረ የጠቆሙት።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025