የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በመንግስት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች የሀገርን እድገትና የህዝብን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ናቸው - የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች

Jun 20, 2025

IDOPRESS

ጎንደር፤ ሰኔ 12/2017(ኢዜአ)፡- በመንግስት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች የሀገርን እድገትና የህዝብን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሆናቸውን የተለያዩ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ተናገሩ።

ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ የተለያዩ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት በጎንደር ከተማ የተከናወኑ እና በመከናወን ላይ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡


በጉብኝቱ ላይ ከተገኙት መካከል የአፋር አብዮታዊ ዴሞክራሲ አንድነት ግንባር ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር መሀመድ አወል፤ በሁሉም አካባቢዎች የተጀመሩ የልማት ስራዎች ትልቅ ተስፋ የሰነቁ ናቸው ብለዋል።

በጎንደር ከተማ የተመለከትናቸው የኮሪደር ልማትን ጨምሮ ሌሎች ዘርፈ ብዙ የልማት ተግባራት የከተማዋን ከፍታ የሚያስቀጥሉ መሆናቸውን አንስተዋል።

የመገጭ የመስኖ እና የመጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክት ለህዝቡ የልማት ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ መሆኑን ጠቅሰው ሌሎች የልማት ስራዎችም ትልቅ ትርጉም አላቸው ብለዋል።

በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ፍትሃዊ ልማትና የዜጎች ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች የሚደነቁ መሆናቸውን ገልጸው በተጠናከረ መልኩ ሊቀጥሉ ይገባል ነው ያሉት።

በክልሉ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እውን በማድረግ በኩል የመንግስት ጥረት እንዳለ ሆኖ የሕዝቡ ተሳትፎና እገዛ ወሳኝነት እንዳለው አንስተዋል።


የሕብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ እጸገነት ተስፋዬ፤ በጉብኝታችን ሀገርን ወደ ዕድገት የሚያሸጋግሩ እና ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ተመልክተናል ብለዋል።

የአጼ ፋሲል አብያተ መንግስት እድሳትና ጥገና ስራ መንግስት ታሪክና ቅርስን ጠብቆ ለትውልድ ለማሻገር ያለውን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

በጎንደር ከተማ በፌደራልና በክልሉ መንግስት ድጋፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶች የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች የመፍታት አቅም ፈጥረዋል ያሉት የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው ናቸው፡፡


ግንባታቸው እየተፋጠነ የሚገኘው ሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት የአጼ ፋሲል አብያተ መንግስት እድሳትና ጥገና እንዲሁም የመገጭ የመስኖና የመጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ሕዝቡና ከተማ አስተዳደሩ ተቀናጅተው የድርሻቸውን እየተወጡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከሀገሪቱ የተውጣጡ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት ጉብኝት ትልቅ መነሳሳትንና ከተማዋን በስፋት ለማስተዋወቅና መልካም ገጽታዋንም ለማጉላት ምቹ አጋጣሚ የፈጠረ ነው ብለዋል፡፡

የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮቹና አባላቱ በከተማው በቅርቡ ተጠናቆ ለአገልግሎት የበቃውን የፒያሳ ኮሪደር ልማት ጨምሮ የአጼ ፋሲል አብያተ መንግስት እድሳትና ጥገና ስራ እንዲሁም የመገጭ የመስኖና የመጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክቶች የግንባታ ሂደትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025