የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በ2017 ብሔራዊ የሳይበር ስልጠና መሳተፍ የሚፈልጉ ባለተሰጥኦዎች እስከ ግንቦት 24 እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀረበ

May 28, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ግንቦት 19/2017 (ኢዜአ)፦በ2017 ብሔራዊ የሳይበር ስልጠና መሳተፍ የሚፈልጉ ባለተሰጥኦዎች እስከ ግንቦት 24 እንዲመዘገቡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጥሪ አቀረበ።


አስተዳደሩ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ ብሔራዊ የሳይበር ተሰጥኦ ውድድር ከሐምሌ አንድ ጀምሮ እንደሚካሄድ አስታውቋል።


በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሳይበር ልህቀት ማዕከል ዳይሬክተር ቢሻው በየነ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥አስተዳደሩ ባለፉት ሶስት ዓመታት ለታዳጊ ወጣቶች ተከታታይ ስልጠናዎችን እየሰጠ ነው።


የ2017 ብሔራዊ የሳይበር ተሰጥኦ ውድድር በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ4ኛ ጊዜ እንደሚካሄድ ተናግረዋል።


በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙና እድሜያቸው ከ11 ዓመት ጀምሮ በስልጠናው መሳተፍ እንደሚችሉ ገልጸው፥ እስከ ግንቦት 24/2017 ዓ.ም እንዲመዘገቡም ጥሪ አቅርበዋል።


መላው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በዚህ ስልጠና በንቃት እንዲሳተፉ የጠየቁት ዳይሬክተሩ፥ ተመዝጋቢዎች በ https://talent.insa.gov.et በመግባት መመዝገብ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።


በ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ስልጠና የወሰዱ ዜጎች የተሻለ እድል እንዳላቸውም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቷል

ጅግጅጋ፣መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፡- መንግሥት የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ተመለከተ። የኢትዮጵያ ከተሞች የ...

Apr 1, 2026

የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር የልማት አጀንዳ ነው

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር አህጉራዊ የልማት አጀንዳ ...

Mar 26, 2026

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025