
ባህር ዳር፤ ሚያዝያ 29/2017(ኢዜአ)፦ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ዲጂታላይዜሽን አሰራርን በመተግበር ለህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ገለጹ።
ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው እንደገለጹት አስተዳደሩ የዲጂታላይዜሽን አሰራርን በመተግበርና ፈጣን አገልግሎት በመስጠት የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው።
በዚህም የቦታ፣ የቤት፣ የመኪናና ሌሎች ንብረቶችን የያዙ 100ሺህ ፋይሎችን ወደ ኮምፒውተር በማስገባት ዘመኑን የሚመጥን የመረጃ አያያዝ ስርዓት ለመዘርጋት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህም ከተማዋን ስማርት ሲቲ ከማድረግ ጋር ተያይዞ አሰራሮችን ዲጂታላይዝ በማድረግ ለህብረተሰቡ ከብልሹ አሰራር የጸዳና ፈጣን አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ያለመ መሆኑን አስረድተዋል።
በቴክኖሎጂ የተደገፈው አሰራር ተገልጋዮች የተለያዩ ሰነዶችን በሚጠይቁበት ወቅት የሚገጥማቸውን እንግልት እንደሚያስቀር ገልጸዋል።
ፋይሎችን ዲጂታላይዝ የማድረጉ ተግባር እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ በማጠናቀቅ ለዜጎች ፍትሃዊና ቀልጠፋ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
አሁን ላይ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የመሬት ማኔጅመንት(ካዳስተር) ስራ ከፍተኛ በጀት ተመድቦ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመው በዚህም ስለከተማዋ መሬት የተሟላ መረጃ ማግኘት የሚቻልበት ሁኔታ ይፈጠራል ብለዋል።
በተጨማሪም የተቋም ግንባታ ላይ በማተኮር ከተማዋን ለቱሪዝም፣ ለኢንቨስትመንትና ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ ሌሎች የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች እየተከናወኑ እንደሆነም ገልፀዋል።
የባህር ዳር ከተማን ስማርት ሲቲ ማድረግን ታሳቢ ያደረጉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት በየዘርፉ እየተከናወኑ መሆኑን አመልክተዋል።
ጅግጅጋ፣መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፡- መንግሥት የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ተመለከተ። የኢትዮጵያ ከተሞች የ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር አህጉራዊ የልማት አጀንዳ ...
Mar 26, 2026
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025