ነገሌ ቦረና፤ሚያዝያ 28/2017(ኢዜአ )፦በምስራቅ ቦረና ዞን በዘንድሮው የበልግ አዝመራ ከ167 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡
በጽህፈት ቤቱ የሰብል ልማት ባለሙያ አቶ ቦነያ ሁቃ በዞኑ በየዓመቱ ከመጋቢት 15 እስከ ሚያዝያ መጨረሻ የበልግ ወቅት እንደሆነ ገልጸው፤ በዘንድሮ የበልግ እርሻ 158 ሺህ ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ ከእቅዱ በላይ መከናወኑን ተናግረዋል።
በዚህም በዞኑ 8 ወረዳዎች 167 ሺህ ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብል ዓይነቶች በዘር መሸፈኑን አስታውቀዋል፡፡
ከዚህ ውስጥ 60 ሺህ ሄክታር የሚሆነው መሬት በስንዴ ምርጥ ዘር የተሸፈነ ሲሆን ከዚህም ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን ገልጸዋል፡፡
በዞኑ በበልግ ወቅት በብዘት ከተዘሩት ዋና ዋና የሰብል ዓይነቶች ውስጥ ስንዴ፣ ጤፍ፣ በቆሎ፣ ቦለቄ፤ ሰሊጥ እና ማሾ መሆኑን ጠቅሰው በአጠቃላይ በዘንድሮ የበልግ ወቅት ከ2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን ተናግረዋል፡፡
በበልግ አዝመራው ከ147 ሺህ በላይ አርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች በልማቱ መሳተፋቸውንም ገልጸዋል፡፡
በጽህፈት ቤቱ የግብዓት አቅርቦትና ስርጭት ባለሙያ አቶ ገመዳ ሀሰን በዞኑ በበልግ አዝመራው 41 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ጥቅም ላይ መዋሉን ጠቁመዋል፡፡
እንዲሁም ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ ከ14 ሺህ ኩንታል በላይ የምርጥ ዘር ዓይነቶች ጥቅም ላይ መዋሉንም ተናግረዋል።
ምርታማነትን የሚጨምሩ አዳዲስ የግብርና ሜካናይዜሽን አሰራሮች በመመቻቸታቸው ከዘንድሮ የበልግ አዝመራ ከፍተኛ ምርት ይጠበቃል ብለዋል፡፡
ከአዳዲስ አሰራሮቹ መካከል የእርሻ ትራክተር አቅርቦት፣ የኩታ ገጠም አስተራረስ፣ የግብዓት አቅርቦት እና የታረሰ መሬት ብዛት ዋና ዋናዎቹ እንደሆኑ ጠቅሰዋል፡፡
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025