
ባህርዳር ፤ መጋቢት 10/2017(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል ለመጪው መኸር ጥራቱ የተጠበቀ ዘር ለአርሶ አደሩ ለማቅረብ ትኩረት መደረጉን የክልሉ የግብርና ጥራትና ደህንነት ባለስልጣን አስገነዘበ ።
አርሶ አደሩ የዘር ጥራት ማረጋገጫ የተለጠፈበትን ትክክለኛ ዘር ለይቶ ሊጠቀም እንደሚገባም ባለስልጣኑ አሳስቧል።
በባለስልጣኑ የዘር ጥራትና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ጉርሜሳ እጀታ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት በክልሉ በባለፈው የምርት ዘመን በ12ሺህ 791 ሄክታር መሬት ላይ 18 አይነት የሰብል ዘር የማባዛት ስራ ተከናውኗል።
የዘር ብዜት ስራውም በመንግስት፣ በድርጅቶች፣ በዩኒየኖች፣ በምርምር ማዕከላት፣ በዩኒቨርስቲዎችና በግልለሰቦች ደረጃ መከናወኑን ገልጸዋል።
በማባዣዎች ከተመረተው ዘር ውስጥ 220ሺህ 371 ኩንታል ዘር ጥራቱን ጠብቆ መሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል ።
ከተሰበሰበው ውስጥም 190 ሺህ ኩንታል ዘር ተበጥሮ ለአርሶ አደሩ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑንም አመልክተዋል።
የተበጠረውን ዘር በላብራቶሪ በማረጋገጥ የጥራት ማረጋገጫ የተለጠፈበት መሆኑን ጠቁመው የበቆሎ፣ ስንዴ፣ ጤፍና ሌሎች የሰብል አይነቶች ይገኙበታል ብለዋል።
አርሶ አደሩም በመጪው የመኽር ወቅት የዘር ጥራት ማረጋገጫ የተለጠፈበትን ትክክለኛ ዘር በመጠቀም የሰብል ምርታማነትን እንዲያሳድግ መልእክት አስተላልፈዋል።
ባለፈው ምርት ወቅት በበቆሎ ዘር ብቻ ተለጥፎ ይቀርብ የነበረው የጥራት ማረጋገጫ ዘንድሮ በሁሉም የሰብል አይነቶች በመለጠፍ የሚቀርብ መሆኑን አስታውቀዋል።
ጅግጅጋ፣መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፡- መንግሥት የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ተመለከተ። የኢትዮጵያ ከተሞች የ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር አህጉራዊ የልማት አጀንዳ ...
Mar 26, 2026
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025