
አዲስ አበባ፤ የካቲት 13/2017(ኢዜአ)፦ በሸገር ከተማ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት 14 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን የከተማዋ አስተዳደር ከንቲባ ተሾመ አዱኛ(ዶ/ር) ገለጹ።
የከተማ አስተዳደሩ ለታማኝ ግብር ከፋዮች ያዘጋጀው የእውቅናና የሽልማት መርሃ ግብር ዛሬ ተካሂዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የከተማዋ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ(ዶ/ር) እንደገለጹት ዘመናዊ፤ የበለጸገና ለኑሮ ምቹ የሆነ ከተማን ለመፍጠር ዜጎች ግብራቸውን በጊዜውና በአግባቡ መክፈል ይኖርባቸዋል።

ሸገር ከተማ ከመቋቋሟ በፊት ሲሰበሰብ የነበረው ገቢ ከ6 ቢሊዮን ብር ያልበለጠ እንደነበር አስታውሰው የከተማዋን መቋቋም ተከትሎ ባለፉት ሁለት ዓመታት 16 ነጥብ 5 በሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን ተናግረዋል።
ይህም ከከተማዋ የሚገኘው ገቢ በየጊዜው እየተሻሻለ ስለመምጣቱ ማሳያ ነው ብለዋል።
እንደ ከንቲባው ገለጻ በተያዘው ዓመት ከከተማዋ ከ27 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ ባለፉት ስድስት ወራት በተደረገ እንቅስቃሴ 14 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ተችሏል።
ሸገር ከተማ የኢኮኖሚ ማዕከል እንደመሆኗ፣ ካለው የመሬት ስፋትና ከሚያስፈልገው መሰረተ ልማትና የልማት ሥራዎች አንጻር ገቢው የሚፈለገውን ያህል እንዳልሆነም ገልጸዋል።
ከተማዋ የምታመነጨውን ገቢ አሟጦ በመሰብሰብ ልማቷን ለማፋጠንና ነዋሪዎቿን ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ከንቲባው አስታውቀዋል።
በከተማዋ ታማኝና ግንባር ቀደም ግብር ከፋይ በመሆን ዛሬ የተሸለሙትን የንግድ ማህበረሰብ አባላት ከንቲባው አመስግነው፣ ከተማ አስተዳደሩ በቀጣይ በጋራ አብሮ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።

በሸገር ከተማ አስተዳደር የገቢዎች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ መልካሙ አምባው በበኩላቸው በበጀት ዓመቱ ከመዘጋጃ ቤታዊ ቀጥተኛና ቀጥተኛ ካልሆኑ የገቢ አርዕስቶች የግብር ገቢ መሰብሰቡን ተናግረዋል።
የግብር አሰባሰቡን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ፣ ግብርን በወቅቱና በአግባቡ መክፈል ባለው ጠቀሜታ ላይ የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ እንዲሁም የተሻሻሉ የታክስ ህጎችን በመተግበር የተሻለ ገቢ በፍጥነት ለመሰብሰብ ተችሏል ብለዋል።
በከተማው በመጀመሪያው ስድስት ወራት የተሰበሰበው ገቢ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ብልጫ እንዳለውም ጠቁመዋል።
ጅግጅጋ፣መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፡- መንግሥት የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ተመለከተ። የኢትዮጵያ ከተሞች የ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር አህጉራዊ የልማት አጀንዳ ...
Mar 26, 2026
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025