ጎንደር፤ የካቲት 10/2017(ኢዜአ)፡- የጎንደር ከተማ የኮሪደር ልማት እና የቅርስ ዕድሳት ሥራዎች የሠላም ጥረቶችና ውጤቶች ማሳያ እንደሆኑ የሠላም ሚኒስትር ዴዔታ ከይረዲን ተዘራ(ዶ/ር) ገለጹ።
ሚኒስትር ዴዔታው በቅርቡ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት የሆነውን የከተማውን የፒያሳ አካባቢ የኮሪደር ልማት፣ የአጼ ፋሲል አብያተ መንግስትን የቅርስ ጥገናና እድሳት ሥራ ጎብኝተዋል፡፡
በዚሁ ወቅት እንዳሉት በኢትዮጵያ የከተሞች ታሪክ ውስጥ ጎንደር ከተማ ጉልህ የኪነ ጥበብ፣ የኪነ ሕንጻና የሥነ መንግስት ታሪክ አላት።
የታሪካዊ ቅርሶች ዕድሳትና ጥገና ሥራ ትውልዱ የነገን ብሩህ ተስፋ አሻግሮ እንዲያይና ተስፋውንም ጠብቆ ለመጪው ትውልድ እንዲያስተላልፍ ምቹ የታሪክ ዐውድ የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡
ጎንደር የታሪክ፣ የባህል፣ የእምነት፣ የአብሮነትና የፍቅር እምቅ ፀጋዎች ባለቤትና ሙዚየም መሆኑዋን አውስተው፤ የቀደመ ታሪኳን የሚመጥን የልማት ዕድል እንድታገኝ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
በጎንደር እየተካሄደ ያለው የኮሪደር ልማትና የቅርስ ዕድሳት ሥራ የሠላም ጥረቶችና ውጤቶች ማሳያ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ሠላምና ልማት የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ገጽታዎች ናቸው ብለዋል፡፡
በሀገራችን ዘላቂ ሠላም እየተገነባ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ህዝቡ የሠላሙና የልማቱ ባለቤት ራሱ መሆኑን ተገንዝቦ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የኮሪደር ልማቱ፣ የቅርስ ጥገናና እድሳት ሥራው ተቀዛቅዞ የቆየውን የከተማውን የቱሪዝም ዘርፍ በማነቃቃት ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው ያሉት የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ ደብሬ የኋላ ናቸው፡፡
የኮሪደር ልማት የሥራ እድል ከመፍጠር ጀምሮ የከተማው ነዋሪዎች አማራጭ የመዝናኛና የማረፊያ አረንጓዴ ሥፍራዎች ተጠቃሚ እንዲሆን ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ነው ብለዋል፡፡
የልማት ሥራዎቹ የህብረተሰቡን የሥራ ባህል በተጨባጭ የቀየሩና የይቻላል ስሜትንም በወጣቱ ዘንድ ማስረጽ የተቻለበት ብለዋል።
በጉብኝቱ ላይ የከተማ አስተዳደሩ አመራር አባላት፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አስራት አፀደወይን(ዶ/ር) እና የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንቶች ተሳትፈዋል፡፡
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025