የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

<p>ኢንስቲትዩቱ በተመራማሪዎቹ ያሰራቸውን ማሽኖች ለክልሎች አበረከተ</p>

Feb 7, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ጥር 29/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት በተመራማሪዎቹ ያሰራቸውን የእንጨትና የብረት ቅርጽ ማውጫ ማሽኖች ለአምስት ክልሎች አስረከበ።


የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ በርክክቡ ወቅት እንደገለጹት፤ ማሽኖቹ በተቋሙ ባለሙያዎች የለሙና በራስ አቅም የተሰሩ ናቸው።

በኢንስቲትዩቱ የተሰሩ አምስት የፕላዝማ እና ራውተር ሲ. ኤን. ሲ ማሽኖችን ለአማራ፣ ትግራይ፣ ሲዳማ፣ አፋር እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ነው ያስረከበው።

ማሽኖቹ በብረትና እንጨት ላይ ቅርጾችን ለማውጣት የሚያገለግሉ መሆናቸውን ገልጸው፤ በክልሎች ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ የሚውሉ መሆኑንም ተናግረዋል።

በማሽኖቹ የሚጠቀሙት ዜጎች ቴክኖሎጂውን በማልማትና በማባዛት በሺዎች የሚቆጠሩ የስራ እድሎችን መፍጠር እንዳለባቸው ነው ያሳሰቡት።

ኢንስቲትዩቱ በአሁኑ ወቅት በሰው ሃይል፣ በአደረጃጀት እና በቴክኖሎጂ የውስጥ አቅሙን በማሳደግ ለአገልግሎት ፈላጊዎች ተደራሽ ለመሆን እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

በተያዘው አመት የስፔስና የጂኦስፓሻል መረጃዎችን ጥቅም ላይ ከማዋል አኳያም በርካታ ሴክተሮችን መመስረቱን አንሰተዋል።

የክልሎቹ ተወካዮች በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ ማሽኖቹን ከማስረከብ ባለፈ በአጠቃቀሙ ላይ ስልጠና እንዲወስዱ ማድረጉን ተናግረዋል።

ኢንስቲትዩቱ ቴክኖሎጂውን ጥቅም ላይ ከማዋል ባለፈም ቀጣይነት ያለው ክትትልና ድጋፍ እንዲያደርግላቸውም ነው የጠቆሙ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቷል

ጅግጅጋ፣መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፡- መንግሥት የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ተመለከተ። የኢትዮጵያ ከተሞች የ...

Apr 1, 2026

የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር የልማት አጀንዳ ነው

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር አህጉራዊ የልማት አጀንዳ ...

Mar 26, 2026

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025