
አዲስ አበባ፤ ጥር 28/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ከስደትና ስደት ተመላሾች ጋር በተያያዘ እያከናወነች ያለችውን ጥረት ኔዘርላንድስ እንደምትደግፍ የሀገሪቱ የፍትህና ደህንነት ሚኒስቴር የአለም አቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክተር ሮብ ቫን ባህሆቨን ገልፀዋል።
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት በዋና ዳይሬክተሩ የተመራ ልዑክን ተቀብለው አነጋግረዋል።
በውይይታቸውም ኢትዮጵያ ከስደትና ስደት ተመላሾች ጋር በተያያዘ እያከናወነች ያለችውን ተግባር በሚመለከትና በቀጣይ ከኔዘርላንድስ ጋር በዘርፉ ያሉ ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ገለፃ አድርገዋል።

በተጨማሪም ተቋሙ በሪፎርም ሂደት ላይ መሆኑንና የሚሰጡ አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ ለማደራጀት በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ማስረዳታቸውን ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
የኔዘርላንድስ የፍትህና ደህነነት ሚኒስቴር የአለም አቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክተር ሮብ ቫን ባህሆቨን ኢትዮጵያ ከስደትና ስደት ተመላሾችን በሚመለከት እያከናወነች ያለችው ስራ የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል።
ሀገራቸው በዚህ ረገድ ኢትዮጵያን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን ማረጋገጣቸውም ተጠቅሷል።
ሁለቱ አካላት በተለይም በአቅም ግንባታ ዘርፍ እና ተቋሙ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ይበልጥ ቀልጣፋ ከማድረግ አኳያ በጋራ ሊሰሩ በሚገቡ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውም ተመላክቷል፡፡
ጅግጅጋ፣መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፡- መንግሥት የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ተመለከተ። የኢትዮጵያ ከተሞች የ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር አህጉራዊ የልማት አጀንዳ ...
Mar 26, 2026
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025