
አዲስ አበባ፤ጥር 5/2017(ኢዜአ)፡-የሳዑዲ ጎልድ ሪፋይነሪ ኩባንያ (Saudi Gold Refinery Co) በኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ የኢንቨስትመንት ስራ ለመጀመር የሚያስችል እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታወቀ።
በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ከድር (ዶ/ር) ከኩባንያው ባለቤት ሱሌይማን ሳሌህ አሎታይም ጋር በሪያድ ተወያይተዋል።
ውይይቱ ኩባንያው በኢትዮጵያ ማዕድን ዘርፍ ኢንቨስት ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።
አምባሳደር ሙክታር፥ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የማዕድን ክምችት ያላት ሃገር መሆኗንና መንግስት በዘርፉ የተለያዩ ማበረታቻዎችን ጨምሮ ምቹ የኢንቨስትመንት ምህዳር ለመፍጠር የሚያስችሉ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ኩባንያው በዘርፉ ያለውን ልምድ እና ቴክኖሎጂ በመጠቀም በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርግ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ኤምባሲውም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አመልክተዋል።
የሳዑዲ ጎልድ ሪፋይነሪ ኩባንያ (Saudi Gold Refinery Co) ሱሌይማን ሳሌህ አሎታይም ኩባንያቸው በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው አመልክተዋል።
ኩባንያው በማዕድን ዘርፍ ስራውን ለማስጀመር የሚያስችል እንቅስቃሴ እንደጀመረ መግለጻቸውን በሪያድ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
ጅግጅጋ፣መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፡- መንግሥት የከተሞችን እድገትና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ተመለከተ። የኢትዮጵያ ከተሞች የ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር አህጉራዊ የልማት አጀንዳ ...
Mar 26, 2026
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025