🔇Unmute
ነቀምቴ፤ ጥር 8/2018 (ኢዜአ)፡- በበጀት ዓመቱ ያለፉት ወራት ከምሥራቅ ወለጋ ዞን 30 ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ደረጄ ነጋሳ ገለጹ።

በበጀት ዓመቱ በቡና ከለማው 47 ሺህ ሔክታር ከ73 ሺህ ቶን በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑንም ተናግረዋል።
ከዚህም 292 ቶን የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ መታቀዱን እና እስካሁን 30 ቶን ምርት መቅረቡን ነው ለኢዜአ ያረጋገጡት።

የቡና ጥራትን ከማስጠበቅ ጎን ለጎን ከቡና ግብይት ጋር የተያያዙ ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን የመከላከል ሥራ ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ እየተከናወነ መሆኑንም አስታውቀዋል።
አርሶ አደሩ ያመረተውን ምርትም በኅብረት ሥራ ዩኒየኖች በኩል ለገበያ እንዲያቀርብ እየተደረገ ስለመሆኑም ተናግረዋል።
የቡና ምርት ለመሰብሰብ የቡና አምራቾችን እና ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ እየተሠራ መሆኑንም ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025