🔇Unmute
ሚዛን አማን፤ ህዳር 16/2018(ኢዜአ)፦ የተቀናጀ የገጠር ኮሪደር ልማትን በመተግበር የኑሮ ዘይቤያቸውን እያሻሻሉ መሆኑን በቤንች ሸኮ ዞን የሼይ ቤንች ወረዳ አርሶ አደሮች ተናገሩ።
አርሶ አደሮቹ ከዚህ ቀደም በልማድ የሚያከናውኑትን የግብርና ልማት ከመቀየር ባለፈ አካባቢያቸውን ጽዱና ለኑሮ ምቹ እያደረጉ መምጣታቸውን ተናግረዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሀሳብ አመንጨኒት በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች የተጀመረው የገጠር ኮሪደር ልማት የአርሶ አደሩን ሕይወት በሚቀይር መልኩ እየተተገበረ ነው።

በዚሁ ኢኒሼቲቭ ወደ ሥራ የገቡት በሼይ ቤንች ወረዳ የኩሻ ቀበሌ አርሶ አደር ጥላሁን ኪዳኔ በአዲስ አበባ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ሥራ ከግብርና ሥራ ጋር በመተሳሰር እስከ ቀበሌ በመውረዱ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በቤታቸው ፊት ለፊት የነበረውን ቆሻሻ ስፍራ በማጽዳት መኖሪያ ግቢያቸውን ከነአጥሩ በማስዋብ ለኑሮ ምቹ ማድርጋቸውን ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ወደ ተቀናጀ የግብርና ሥራ መግባታቸውን የገለጹት አርሶ አደሩ፣ ከዚህ ቀደም ከሚሠሩት የእርሻ ሥራ ባሻገር የገጠር ኮሪደር ልማትን ከሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር ጋር በማስተሳሰር እያከናወኑ መሆኒንም ጠቁመዋል።
በዚህም የወተት ላም እርባታ፣ የእንቁላልና ዶሮ ልማት ስራዎችና ሌሎች የልማት ሥራዎችን በማከናወን ተጠቃሚነታቸውን እያሳደጉ መምጣታቸውን ነው የገለጹት።
በተቀናጀ የግብርና ሥራቸው የሚያገኙትን ምርት ለቤት ውስጥ ፍጆታ ከማዋል ባለፈ ገቢያቸውን እያሳደጉና ለከተማ ኢንቨስትመንት ሥራ እያዋሉ መሆናቸውንም ጨምረው ተናግረዋል።

ሌላው የቀበሌው ሞዴል አርሶ አደር ታዬ ባሉስ በመንግስት የተጀመረውን የገጠር ኮሪደር ልማት እሳቤ ተረድተው ወደ ተግባር ከገቡ አርሶ አደሮች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።
የመኖሪያ ግቢያቸውን ንጽህናና ውበት ከማስጠበቅ ጀምሮ የከብቶች ማደሪያ ቤት፣ የምግብ ማብሰያና የዶሮ ቤትን ከሰው መኖሪያ ለይቶ በማዘጋጀት ኑሯቸውን እያሻሻሉ መምጣታቸውን ተናግረዋል።
በግብርና ባለሙያዎች ታግዘው ከሚያከናውኑት የሰብልና የጓሮ አትክልት ልማት ቤተሰቦቻቸውን እያስተዳደሩና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እያሳደጉ መምጣታቸውን ገልጸዋል።

ባለቤታቸው ወይዘሮ ሙሉነሽ ዶርሳም የመኖሪያ ቤታቸውን ዙሪያ አጽድቶ ከማሳመር ጀምሮ ካለሙት ጎደሬና ሌሎች የጓሮ አትክልቶች ተጠቃሚነታቸውን እያሳደጉ መምጣታቸውንም ተናግረዋል።

የሼይ ቤንች ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ይታገሱ ታመነ በወረዳው 67 ኪሎ ሜትር የገጠር ኮሪደር ልማት ሥራ መከናወኑን አስታውቀዋል።
በልማቱም ከመንገድ ማስፋትና አጥር ሥራ ባሻገር አርሶ አደሩ በጓሮው ማር፣ ወተት፣ ዶሮ፣ እንቁላልና ሌሎች የግብርና ምርቶችን በማምረት የተሻለ ተጠቃሚ እንዲሆን በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025