🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ህዳር 3/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለአምራች ኢንዱስትሪው ማንሰራራት መሰረት መጣሉን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ ተገንብተው የተጠናቀቁና በግንባታ ላይ ያሉ የተለያዩ የማምረቻ ፋብሪካዎችን ጎብኝተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት፤ የዘይት ፋብሪካና የአልሚ የምግብ ማቀነባበርያ ፋብሪካን መጎብኘታቸውን አንስተዋል።
በዚህም ፋብሪካዎቹ አለም አቀፍ ደረጃቸው የጠበቁ ምርቶችን በማምረት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ እያደረጉ እንደሚገኙ መመልከታቸው ጠቁመዋል።
በተለይም ከዘይት ምርት የሚገኘውን ተረፈ ምርት ከሀገር ውስጥ ፍጆታ ባሻገር ወደ ውጭ በመላክ የተሻለ ገቢ እየተገኘ መሆኑን አንስተዋል።
አንዳንዶቹ ወደ ግል የኢንዱስትሪ መንደርነት የሚያድጉ እንደሆኑም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምረው ገልፀዋል።
እንዲሁም የቢራ ገብስን የሚተካ የበቆሎ ግብዓትን የሚጠቀም ፋብሪካ መጎብኘታቸውን ገልፀው፤ ፋብሪካው በበቆሎ አምራች ገበሬዎችንና በኢንዱስትሪው መካከል ትሥሥርን የሚፈጥር፤ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርቶች የሚተካ ነው ብለዋል።
በዚህም ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል የሚፈጥር እንደሆነ ነው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለፁት።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብታቸው የተመለከቱት የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በማምረት ለትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፉ ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል።
እንዲሁም በጥቃቅንና አነስተኛ ለሰለጠኑ ባለሙያዎች ተጨማሪ የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት የስራ እድል መፍጠር መቻሉና የራሳቸውን ድርጅት እንዲከፍቱ እገዛ መደረጉ የሚበረታታ ተግባር መሆኑን ጠቅሰዋል።
በደብረ ብርሃን ከተማ የተመለከቷቸው የልማት ስራዎች የኢትዮጵያን ብልፅግና አይቀሬነት የሚያረጋግጡ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
በከተማው ትላልቅ ኢንዱስትሪዎች በመገንባት ላይ መሆናቸውን የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አካባቢው ሰላማዊ መሆኑ ምርታማነት እንዲነቃቃ ማድረጉን መመልከታቸውን አስታውቀዋል።
በከተማዋና በዙሪያዋ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማፋጠን የክልሉና የፌዴራል መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የሀገር ውስጥ ምርትን በከፍተኛ ሁኔታ በማነቃቃት ባለሀብቱ እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ወደ ሥራ እንዲገቡ ዕድል መፍጠሩንም አስረድተዋል፡፡
እሴት የተጨመረባቸውን ምርቶች በማምረት ወደ ውጪ ለመላክ የሚያስችሉ አመርቂ ተግባራት መከናወናቸውን በማድነቅ ሥራዎቹን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025