🔇Unmute
ገንዳውኃ፤ ጥቅምት 22/2018 (ኢዜአ):-በምዕራብ ጎንደር ዞን የእንስሳት ምርታማነትን ይበልጥ ለማሳደግ የሚያግዝ ግማሽ ሚሊዮን ቶን የሚጠጋ መኖ መሰብሰቡን የዞኑ እንስሳትና አሣ ሃብት ተጠሪ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
በጽሕፈት ቤቱ የእንስሳት ተዋፅኦ ምርት ባለሙያ አቶ ወርቄ ዱቤ፤ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብሩ ለእንስሳት ጤና አጠባበቅና ምርታማነት ትኩረት እንዲሰጥ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ለኢዜአ ተናግረዋል።
በዚህም በበጀት ዓመቱ በአካባቢው ከሚገኘው የሣር ድርቆሽና ከኢንዱስትሪ ውጤቶች ከ2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ቶን በላይ መኖ ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
እስካሁን በተደረገው ጥረትም ግማሽ ሚሊዮን ቶን የሚጠጋ መኖ በመሰበሰብ ማከማቸት መቻሉን አስታወቀዋል።
ይህም የእንስሳት ጤናን በመጠበቅ በበጀት ዓመቱ ከ121 ሚሊዮን ሊትር በላይ ወተትና ከ12ሺህ 540 ቶን በላይ ሥጋ ለማምረት የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት እንደሚያግዝ አስረድተዋል።
እስካሁንም ከ22 ሚሊዮን ሊትር በላይ ወተትና ከአንድ ሺህ 774ቶን በላይ ሥጋ በማምረት ለቤት ውስጥ ፍጆታና ለአካባቢው ማህብረሰብ በማቅረብ አርሶ አደሩ ተጠቃሚ ሆኗል ብለዋል።
እንደ ባለሙያው ገለጻ ፤ በዞኑ በሚገኙ ወረዳዎች ለእንስሳት እርባታ ምቹና ለመኖ ልማት የሚውል መሬት መኖሩ የወተትና የሥጋ ምርትን ለመጨመር እያስቻለ ነው።
በአካባቢው የተሻለ የሥጋና የወተት ምርት የሚሰጡ የዳልጋ ከብት ዝርያዎችን በዘመናዊ መንገድ በማባዛት ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
በዞኑ ገንዳውኃ ከተማ በእንስሳት እርባታ ሥራ ላይ ከተሰማሩት ነዋሪዎች መካከል አቶ ቢሰጥ ካሴ በሰጡት አስተያየት፤ በአካባቢው የመኖ ልማትን በዘመናዊ መንገድ አከማችተው ላሞቻቸውን እየቀለቡ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዚህም ቀደም ሲል ከአንድ ላም ያገኙት የነበረውን ከአንድ ሊትር ያልበለጠ የወተት ምርት ወደ ሦስት ሊትር በማሳደግ ተጠቃሚ እንደሆኑ ገልጸዋል።
በዞኑ ቋራ ወረዳ የገለጎ ከተማ ነዋሪ አቶ አየነው እሸቴ በበኩላቸው፤ የወተት ላሞችን ጤና አጠባበቅና የመኖ አቅርቦትን በማሻሻል በወተት ምርት ተጠቃሚነታቸው እያደገ መሆኑን ተናግረዋል።
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025